ዘፍጥረት 25:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ዚምራንን፥ ዮቅሻንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የሽቦቅን፥ እና ሹሐን ወለደችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፦ ዘምራንን፣ ዮቅሳንን፣ ሜዳንን፣ ምድያምን፣ የስቦቅንና ስዌሕን ወለደችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ዚምራንን፥ ዮቅሻንን፥ መዳንን፥ ምድያምን፥ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ዘንበሪን፥ ዮቃጤንን፥ ሜዳንን፥ ዮብቅን፥ ምድያምንና ሴሂን ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ዘምራንን ዩቅሳንን ሜዳንን ምድያምን የስቦቅን ስዌሕን ወለደችለት። |
የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም ጥቂቶች ሰዎች ከእነርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ግብጽ ተጉዘው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም ለሀዳድ መሬትና አንድ መኖሪያ ቤት ሰጥቶ ምግብ ፈቀደለት።
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።
ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፦ “በሬ የለመለመውን የሣር መስክ ግጦ እንደሚጨርስ ይህ ጭፍራ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ አሁን ይጨርሳል” አላቸው። በዚያን ጊዜም የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፥
ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት።