ዓይኑን አንስቶም ሴቶችንና ልጆችን ባየ ጊዜ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” አለ። እርሱም፦ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።
መክብብ 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሠኘበትና በአግባብ ካልተቀበረ፣ ከርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ፥ አንድ ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ ረጅም ዕድሜ አግኝቶ ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖርም፥ እንዲደሰትበት ከሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ድርሻውን ሳያገኝ ቀርቶ በመጨረሻም በክብር ለመቀበር ሳይበቃ ቢቀር፥ እኔ ስለ እርሱ አዝናለሁ፤ ከእንደዚህ ያለውም ሰው ይልቅ በእናቱ ማሕፀን ሞቶ የተወለደ ጭንጋፍ ይሻላል አልኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ ብዙ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም ብዙ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፥ “ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነፍሱም መልካምን ባትጠግብ መቃብርንም ባያገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፦ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ። |
ዓይኑን አንስቶም ሴቶችንና ልጆችን ባየ ጊዜ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” አለ። እርሱም፦ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።
ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
ብዛታቸው ሰባ የሚሆን የአክዓብ ልጆች በሰማርያ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ የደብዳቤውን አንዳንድ ቅጂ ለከተማይቱ ገዢዎች፥ ለታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና የአክዓብን ተወላጆች ለሚያሳድጉ ሞግዚቶች ሁሉ ላከ፤ የደብዳቤውም ቃል፥
ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ፤ ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስልሳ ቁባቶች ነበሩት፥ ሀያ ስምንት ወንዶችና ስልሳ ሴቶች ልጆች ወለደ።
ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከእርሱም በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይኖረውም፥ ሬሳውም በቀን ለፀሐይ ሐሩርና በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል።
በወደዱአቸውና ባገለገሉአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።
የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰውን ልጅ አልፎ ለሚሰጥ ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር።”