መክብብ 6:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እግዚአብሔር ለሰው ሀብትን፥ ንብረትንና ክብርን ሰጠው፥ ከወደደውም ነገር ሁሉ ለነፍሱ አልጐደለውም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበላዋል እንጂ ከእርሱ ይበላ ዘንድ እግዚአብሔር ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይህም ከንቱና ክፉ ደዌ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ሰው ልቡ የሚሻውን እንዳያጣ፣ አምላክ ባለጠግነትን፣ ሀብትንና ክብርን ይሰጠዋል፤ አምላክ ግን እንዲደሰትበት ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይልቁን ባዕድ ይደሰትበታል። ይህም ከንቱ፣ እጅግም ክፉ ነገር ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እግዚአብሔር ለሰው ምድራዊ ሀብትንና ብልጽግናን ክብርንም ሁሉ ይሰጠዋል፤ ከሚያስፈልገውም ነገር ሁሉ ምንም አያጐድልበትም፤ ይሁን እንጂ በሚሰጠው ሀብት ሁሉ አይደሰትበትም፤ ይልቁንም እርሱ ደክሞ ያፈራውን ሌላ ሰው ይደሰትበታል። ይህም ከንቱና እጅግ የከፋ በደል ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እግዚአብሔር ለሰው ሀብትንና ጥሪትን ክብርንም ሰጠው፥ ከወደደውም ሁሉ ለሰውነቱ የከለከላት የለም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበላዋል እንጂ ከእርሱ ይበላ ዘንድ እግዚአብሔር አላሠለጠነውም፤ ይህም ከንቱና ክፉ ደዌ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እግዚአብሔር ለሰው ሀብትንና ጥሪትን ክብርንም ሰጠው፥ ከወደደውም ሁሉ ለነፍሱ አልጐደለውም፥ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበላዋል እንጂ ከእርሱ ይበላ ዘንድ እግዚአብሔር አላሠለጠነውም፥ ይህም ከንቱና ክፉ ደዌ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |