ዘዳግም 2:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሞዓብ ዳርቻ ዔርን ዛሬውኑ ታልፋላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘የሞአብ ክልል በሆነው በዔር በኩል ዛሬውኑ ማለፍ አለባችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ አሮኤርን ታልፋለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ፤ |
ከዚያም ተጉዘው ከአሞራውያን ዳርቻ ትይዩ በተዘረጋው ምድረ በዳ ውስጥ በአርኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና።
ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።
ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ፥ ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ በውጊያም አትጋፈጣቸው።’”
“ቀጥሎም የኤዶምንና የሞዓብን ምድር በመዞር፥ በምድረ በዳው ተጉዞ ከሞዓብ በስተ ምሥራቅ በኩል በማለፍ ከአርኖን ማዶ ሰፈረ፤ የሞዓብም ድንበር አርኖን ስለ ነበር ወደ ሞዓብ ክልል አልገባም።