ዘዳግም 18:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም በልብህ፥ ‘በጌታ ያልተነገረውን መልእክት እንዴት ማወቅ እንችላለን?’ ብትል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም በልብህ፣ “እግዚአብሔር ያልተናገረውን መልእክት እንዴት ማወቅ እንችላለን?” ብትል፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘አንድ ነቢይ የሚናገረው የትንቢት ቃል ከእግዚአብሔር ያልተሰጠ መሆኑን በምን ለይቼ ዐውቃለሁ?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልብህም፦ እግዚአብሔር ያልተናገረውን ቃል እንዴት አውቃለሁ ብትል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በልብህም፦ እግዚአብሔር ያልተናገረውን ቃል እናውቅ ዘንድ እንዴት ይቻለናል? ብትል፥ |
ነቢዩ በጌታ ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገለጸ፥ መልእክቱ ጌታ የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።”
“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንደማትችል፥ እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ‘ነን’ የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤