2 ሳሙኤል 22:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህ፤ ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፥ ትዕቢተኞችን ይመለከታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ትሑታንን ታድናለህ፤ ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፣ ትዕቢተኞችን ይመለከታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትሑቶችን ታድናለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ታዋርዳለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ የተዋረደውን ሕዝብ ታድናለህና፤ የትዕቢተኞችን ዐይኖች ግን ታዋርዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ። |
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እንዲህም አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በፊቴ እራስህን ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደርግህበት፥ ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን!’