Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 5:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሰውም ዝቅ ዝቅ ይላል፤ ሰው ይዋረዳል፤ የእብሪተኛውም ዐይን ይሰበራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሰው ይዋረዳል፤ የሰው ልጅም ዝቅ ዝቅ ይላል፤ የእብሪተኛውም ዐይን ይሰበራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሰው ሁሉ የተዋረደ ጐስቋላ ይሆናል፤ ትዕቢተኛ የነበረውም ሁሉ ይዋረዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ታናሹ ሰውም ይጐ​ሰ​ቍ​ላል፤ ታላቁ ሰውም ይዋ​ረ​ዳል፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሰውም ይጐሰቍላል፥ ሰውም ይዋረዳል፥ የትዕቢተኞችም ዓይን ትዋረዳለች፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 5:15
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህ፤ ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፥ ትዕቢተኞችን ይመለከታል።


የዳዊት የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ ልቤ አይታበይም፥ ዐይኖቼም ከፍ ከፍ አይሉም፥ ለትልልቅ ነገሮች፥ ከዐቅሜም በላይ ለሆኑት አልጨነቅም።


ሕዝቦች ሆይ፥ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፥ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነው።


እንዳትለቅቃቸው አሁንም በሕዝቤ ላይ ትታበያለህ፤


በትዕቢት ከፍ ከፍ ያሉ ዐይኖች ያሉት፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ።


ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤


እነሆ፥ ልዑል እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ፤ በታላቅ ኃይል ቅርንጫፎችን ይቈራርጣል፤ ረጃጅም ዛፎች ይገነደሳሉ፤ ከፍ ከፍ ያሉትም ይወድቃሉ።


ዓለምን ስለ ክፋቷ፤ ክፉዎችንም ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችን እብሪት እሽራለሁ፤ የጨካኞችንም ጉራ አዋርዳለሁ።


የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፤ የተኩራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።


የሰው እብሪት ይዋረዳል፤ የሰውም ኩራት ይወድቃል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤


ሰው ዝቅ ብሏል፤ የሰው ልጅም ተዋርዶአል፤ ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል።


የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደርግህበት፥ ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን!’


ቁጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


በዚያ ቀን በእኔ ላይ አምፀሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም፤ በኩራትሽ የተደሰቱትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ላይ ዳግመኛ አትታበዪም።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች