2 ሳሙኤል 22:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዓቱም አልራቅሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ሕጎች ሁሉ እፈጽማለሁ፤ ሥርዓቱንም ከማክበር ወደ ኋላ አላልኩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበርና፤ ጽድቁም ከእኔ አልራቀምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ከሥርዓቱም አልራቅሁምና። |
“እንዲህም ይሆናል፥ ይህችን ፍርድ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ጌታ አምላካችሁ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳንና ዘላለማዊ ፍቅር ለአንተም ይጠብቅልሃል፥