Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 22:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የጌታን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ ከአምላኬ ክፋት በማድረግ አልተለየሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እኔ የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትያለሁ፤ ፊቴን ከአምላኬ በመመለስ ክፉ ነገር አላደረግሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጠብ​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ በአ​ም​ላ​ኬም አላ​መ​ፅ​ሁ​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 22:22
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥ መንገዴንም የሚጠብቁ ምስጉኖች ናቸው።


ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።


የመዓርግ መዝሙር። ጌታን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።


ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።


እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።


ጌታን ከመከተል የተመለሱትን፥ ጌታን ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።


ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።


በመንገዳቸው እንከን የሌለባቸው፥ በጌታም ሕግ የሚመላለሱ ምስጉኖች ናቸው።


እራሱን ሸንግሎአልና፥ ኃጢአቱን መቀበልና መጥላት ይሳነዋል።


እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”


ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ ጌታንም እንዲህ አለው፦ “ወደ ቁርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”


አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት እኔን ብታገለግል፥ የእኔን ሕግና ሥርዓት ብትጠብቅ፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፥


ለመዘምራን አለቃ ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ ሁሉ እጅ ጌታ ባዳነው ቀን በዚህ መዝሙር ቃል ለጌታ የተናገረው የጌታ ባርያ የዳዊት መዝሙር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች