በዚያም ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ምክር ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጠየቅ ይቆጠር ነበር፤ በዳዊትም ሆነ በአቤሴሎም የአኪጦፌል ምክር ይከበር ነበር።
2 ሳሙኤል 17:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አኪጦፌልም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰው ልምረጥና፥ ዛሬ ሌሊት ተነሥቼ ዳዊትን አሳድደዋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አኪጦፌልም፣ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰው መርጬ፣ በዛሬዪቱ ሌሊት ዳዊትን አሳድደዋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቈይ አኪጦፌል አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዛሬ ማታ ዳዊትን አሳድጄ ለመያዝ እችል ዘንድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች እንድመርጥ ፍቀድልኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አኪጦፌልም አቤሴሎምን አለው፥ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ልምረጥና በዚህች ሌሊት ተነሥቼ ዳዊትን ላሳድድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አኪጦፌልም አቤሴሎምን፦ አሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ልምረጥና በዚህች ሌሊት ተነሥቼ ዳዊትን ላሳድድ። |
በዚያም ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ምክር ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጠየቅ ይቆጠር ነበር፤ በዳዊትም ሆነ በአቤሴሎም የአኪጦፌል ምክር ይከበር ነበር።