Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 17:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በደከመውና በዛለ ጊዜም ሽብር እለቅበታለሁ፤ አብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ ትቶት ይሸሻል፤ ንጉሡን ብቻውን እመታዋለሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜም አደጋ እጥልበታለሁ፤ ሽብር እለቅበታለሁ፤ ከዚያም ዐብሮት ያለው ሕዝብ ሁሉ ትቶት ይሸሻል፤ ንጉሡን ብቻ እመታዋለሁ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ደክ​ሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወ​ድ​ቅ​በ​ታ​ለሁ፤ አስ​ፈ​ራ​ው​ማ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸ​ሻል፤ ንጉ​ሡ​ንም ብቻ​ውን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ደክሞና እጅ ዝሎ ሳለ እወድቅበታለህ፥ አስፈራውማለሁ፥ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸሻል፥ ንጉሡንም ብቻውን እመታዋለሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 17:2
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሶርያ ንጉሥ “በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ” ሲል ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትእዛዝ አስተላለፈ።


ንጉሡና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ።


ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንደሚሻል አታስቡም፤” አላቸው።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ ተብሎ ተጽፎአልና፥ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤


ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ።


ደክመህና ዝለህ በነበርህበት ጊዜ፥ በጉዞ ላይ አግኝተውህ፥ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአብሔርንም አልፈሩም።


አኪጦፌልም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰው ልምረጥና፥ ዛሬ ሌሊት ተነሥቼ ዳዊትን አሳድደዋለሁ፤


ጠላቶቻችንም፦ “በመካከላቸው እስክንገባና እስክንገድላቸው ድረስ፥ ሥራቸውንም እስክናስተጓጉል ድረስ አያውቁም፥ አያዩምም” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች