ያየውም ራእይ እንዲህ ነበር፥ አንድ በፊት ሊቀ ካህናት የነበረ የዋህና ደግ ሰው፥ መልኩ ግሩም፥ ሁኔታው ያማረ፥ አነጋገሩ መልከም የሆነ፥ ከልጅነቱ ጀምሮ በጽድቅ ሥራ የተጠመደ ስለ መላው የአይሁድ ሕዝብ እጆቹን ዘርግቶ ሲጸልይ አየ፤