በጠዋት የፀሐይ ብርሃን በታየ ጊዜ በዚህም በዚያም ውጊያውን ጀመሩ፤ ግማሾቹ በእግዚአብሔር ተማጥነው በጀግንነታቸው እንደሚቀናቸውና ድል እንደሚነሱ ዋስትና ኖሯቸው፥ ሌሎቹ ቁጣቸውን የውጊያው መሪ አድርገው ይዋጉ ነበር።