2 ነገሥት 24:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በናቡከደነፆር የጦር አዛዦች የሚመራው የባቢሎን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ላይ ዘምቶ የከበባትም በዚሁ በዮአኪን ዘመነ መንግሥት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የናቡከደነፆር ጦር አለቆች ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መጥተው ከበቧት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በናቡከደነፆር የጦር አዛዦች የሚመራው የባቢሎን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ላይ ዘምቶ የከበባትም በዚሁ በዮአኪን ዘመነ መንግሥት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የናቡከደነፆር ሠራዊት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ ከተማዪቱም ተከበበች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የናቡከደነዖር ባሪያዎች ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ ከተማይቱም ተከበበች። |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ፥ ጌታ አሳየኝ፥ እነሆም፥ በጌታ መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር።
እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።
አንተም የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር፥ መዳፍህን በመዳፍህ ምታ፥ የተገደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደጋግም የሚከብባቸው የተገደለ የታላቅ ሰው ሰይፍ ነው።