ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥
1 ጴጥሮስ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእናንተም ቢሆን ውበታችሁ ውጫዊ የሆነ፥ ሹሩባ በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና የከበረ ልብስ በመልበስ አይሁን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን፣ ይኸውም፣ ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእናንተ ውበት ጠጒርን በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና፥ የከበረ ልብስ በመልበስ በውጪ በሚታየው ጌጥ አይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥ |
ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥
እኔም፦ ‘አንቺ የማን ልጅ ነሽ?’ ብዬ ጠየቅኋት። እርሷም፦ ‘ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ’ አለች፥ ቀለበትም አደረግሁላት፥ ለእጆችዋም አምባሮች አደረግሁላት።
በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር።
ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር እቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”
ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ።
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።
አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።
አንቺም የተደመሰስሽ ሆይ! ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በኩል ተኩለሽ በተቆነጀሽ ጊዜ፥ በከንቱ እራስሽን ታጌጫለሽ፤ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።