Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር እቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እያንዳንዷ ዕብራዊት ከጎረቤቷም ይሁን ዐብራት ከምትኖረው ግብጻዊት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች እንደዚሁም ልብስ እንድትሰጣት ትጠይቅ። እነዚህንም ሁሉ ወስዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ታስጌጧቸዋላችሁ፤ ታለብሷቸዋላችሁም። በዚህም መንገድ የግብጻውያኑን ሀብት በእጃችሁ አግብታችሁ ትወጣላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የዕብራውያን ሴቶች እያንዳንዳቸው ጐረቤት በመሆን አብረዋቸው የሚኖሩትን ግብጻውያን ሴቶች ወርቅ፥ ብርና፥ ጌጣጌጥና ልብስ እንዲሰጡአቸው ይጠይቃሉ፤ ይህንንም ሁሉ ወስዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ታለብሳላችሁ፤ በዚህም ዐይነት ግብጻውያንን በዝብዛችሁ ትወጣላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ነገር ግን እያ​ን​ዳ​ን​ዲቱ ሴት ከጎ​ረ​ቤቷ፥ በቤ​ቷም ካለ​ችው ሴት የብር ዕቃ፥ የወ​ርቅ ዕቃ፥ ልብ​ስም ትዋ​ሳ​ለች፤ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ላይም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ትበ​ዘ​ብ​ዛ​ላ​ችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር ዕቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 3:22
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።


ሎሌውም የብርና የወርቅ ጌጥ ልብስም አወጣ፥ ለርብቃም ሰጣት፥ የከበረ ስጦታንም ለወንድምዋና ለእናትዋ አቀረበ።


ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ የተደናቀፈ አልነበረም።


ወንዱ ከጎረቤቱ ሴቲቱም ከጎረቤቷ የብር ዕቃና የወርቅ ዕቃ እንዲጠይቁ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር።”


ጻድቅ ሰው ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል፥ የኃጢአተኛ ብልጥግና ግን ለጻድቅ ትጠበቃለች።


አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ አንተም ሳትካድ ክህደትን የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትን በተውክ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መካድን በተውክ ጊዜ ትካዳለህ።


በጦር መሣሪያው እሳትን ያነድዳሉ እንጂ እንጨትን ከሜዳ አይሸከሙም፥ ከዱርም አይቆርጡም፤ የዘረፉአቸውን ይዘርፋሉ የበዘበዙአቸውንም ይበዘብዛሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች