ኤርምያስ 2:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 በውኑ ኰረዳ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጣጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን በቍጥር ለማይቆጠሩ ቀናቶች ረስተውኛል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ለመሆኑ ቈንጆ ጌጣጌጧን፣ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን፣ እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ለመሆኑ ኰረዳ ጌጣጌጥዋን፥ ሙሽራም የሙሽርነት ልብስዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ሊቈጠሩ ለማይችሉ ለብዙ ዘመናት ረስተውኛል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 በውኑ ሙሽራ ጌጥዋን ወይስ ድንግል ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠር ወራት ረስቶኛል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን የማይቈጠር ወራት ረስቶኛል። ምዕራፉን ተመልከት |