ይሁዳ የኤሳውን ልጆች በኢዱምያስና በአቅራባቲና ወጋቸው፤ ምክንያቱም እነርሱ የእስራኤልን ሕዝብ ከበው ነበር፤ ደኀና አድርጐ መታቸውና አሸነፋቸው፤ ዕቃዎቻቸውንም ማርኮ ወሰደ።