Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 9:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ሠራ​ዊት በከ​ተ​ማ​ዪቱ መግ​ቢያ በር ሸም​ቀው ቆሙ። እነ​ዚያ ሁለቱ ሠራ​ዊት ግን ወደ ጫካው ተበ​ት​ነው አጠ​ፉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 ከዚያም አቢሜሌክና ዐብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፣ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ከዚያም አቤሜሌክና አብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማይቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፥ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የተመደበው ቡድን የከተማይቱን ቅጽር በር ለመጠበቅ ተጣድፈው ወጥተው በከተማው መግቢያ በር ላይ ቆሙ፤ የቀሩት ሁለቱ ቡድኖች በመስኩ በተገኙት ላይ አደጋ ጥለው ፈጁአቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 አቤሜሌክም ከእርሱም ጋር ያሉት ወገኖች ተጣደፉ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሙ፥ ሁለቱም ወገኖች በእርሻው ውስጥ በነበሩት ሁሉ ላይ ሮጡባቸው፥ መቱአቸውም።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 9:44
5 Referencias Cruzadas  

እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​በ​ላ​ሉና የም​ት​ነ​ካ​ከሱ ከሆነ ግን፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ዳ​ት​ተ​ላ​ለቁ ተጠ​ን​ቀቁ።


ዶግም ዛፎ​ቹን፦ በእ​ው​ነት እኔን በእ​ና​ንተ ላይ ካነ​ገ​ሣ​ች​ሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊ​ባ​ኖ​ስን ዝግባ ካል​በ​ላው ከጥ​ላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለ​ቻ​ቸው።


እን​ዲህ ባይ​ሆን ግን ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰ​ቂ​ማ​ንም ሰዎች፥ የመ​ሐ​ሎ​ን​ንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይ​ሆን ከሰ​ቂማ ሰዎች ከመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ትብ​ላው።”


ሕዝ​ቡ​ንም ወስዶ በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሜ​ዳም ሸመቀ፤ ተመ​ለ​ከ​ተም፤ እነ​ሆም፥ ሕዝቡ ከከ​ተማ ወጡ፤ ተነ​ሣ​ባ​ቸ​ውም፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም በዚያ ቀን ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ጋር ተዋጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ይዞ በእ​ር​ስዋ የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ገደለ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም አፈ​ረሰ፤ ጨውም ዘራ​ባት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos