Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 6:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጌዴ​ዎ​ንም ሄደ፤ የፍ​የ​ሉ​ንም ጠቦት፥ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያም ዱቄት የቂጣ እን​ጎቻ አዘ​ጋጀ፤ ሥጋ​ው​ንም በሌ​ማት አኖረ፤ መረ​ቁ​ንም በም​ን​ቸት ውስጥ አደ​ረገ፤ ሁሉ​ንም ይዞ በዛፍ በታች አቀ​ረ​በ​ለት። ሰገ​ደ​ለ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጌዴዎን ወደ ቤቱ ሄደ፤ የፍየል ጠቦትም ዐረደ፤ አንድ ኢፍ መስፈሪያ ዱቄት ወስዶ ቂጣ ጋገረ። ሥጋውን በቅርጫት፣ መረቁን በምንቸት ይዞ በመምጣት በባሉጥ ሥር ለተቀመጠው አቀረበለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጌዴዎን ወደ ቤቱ ሄደ፤ የፍየል ጠቦትም ዐረደ፤ አንድ ኢፍ መስፈሪያ ዱቄት ወስዶ እርሾ ያልገባበት ቂጣ ጋገረ። ሥጋውን በቅርጫት፥ መረቁን በምንቸት ይዞ በመምጣት በባሉጥ ሥር ለተቀመጠው አቀረበለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ጌዴዎንም ወደ ቤት ገባና የፍየል ጠቦት ዐርዶ አዘጋጀ፤ ዐሥር ኪሎ የሚያኽልም ዱቄት ወስዶ እርሾ ያልገባበት እንጀራ ጋገረ፤ ሥጋውን በመሶብ፥ መረቁን በምንቸት አድርጎ በወርካው ሥር ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር መልአክ ወስዶ አቀረበለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጌዴዎን ገባ የፍየሉንም ጠቦት የኢፍ መስፈሪያም ዱቄት የቂጣ እንጎቻ አዘጋጀ፥ ሥጋውን በሌማት አኖረ፥ መረቁንም በምንቸት ውስጥ አደረገ፥ ሁሉንም ይዞ በአድባሩ ዛፍ በታች አቀረበለት።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 6:19
9 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ በፊ​ት​ህስ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ባሪ​ያ​ህን አት​ለ​ፈው፤


ከዛ​ፉም ሥር ዕረፉ፤ እን​ጀ​ራም እና​ም​ጣ​ላ​ች​ሁና ብሉ፤ ከዚ​ያም በባ​ሪ​ያ​ችሁ ዘንድ ከአ​ረ​ፋ​ችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰ​ባ​ች​ሁት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ልህ እን​ዲሁ አድ​ርግ” አሉት።


“በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረ​ውን ቍር​ባን ስታ​ቀ​ርብ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት፥ የቂጣ እን​ጎቻ ወይም በዘ​ይት የተ​ቀባ ስስ ቂጣ ይሁን።


ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”


ነበ​ል​ባ​ሉም ከመ​ሠ​ዊ​ያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ ነበ​ል​ባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ተመ​ለ​ከቱ፤ በም​ድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ።


ወደ አን​ተም እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ቴ​ንም አም​ጥቼ እስ​ካ​ቀ​ር​ብ​ልህ ድረስ፥ እባ​ክህ፥ ከዚህ አት​ሂድ” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ት​መ​ለስ ድረስ እቈ​ያ​ለሁ” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “ሥጋ​ው​ንና የቂ​ጣ​ውን እን​ጎቻ ወስ​ደህ በዚህ ድን​ጋይ ላይ አኑር፤ መረ​ቁ​ንም አፍ​ስስ” አለው። እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos