Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 14:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቀን ፀሐይ ሳት​ገባ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች፥ “ከማር የሚ​ጣ​ፍጥ ምን​ድን ነው? ከአ​ን​በ​ሳስ የሚ​በ​ረታ ማን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “በጥ​ጃዬ ባላ​ረ​ሳ​ችሁ ኑሮ የእ​ን​ቆ​ቅ​ል​ሼን ትር​ጓሜ ባላ​ወ​ቃ​ች​ሁም ነበር” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በሰባተኛው ቀን ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት የከተማው ሰዎች፣ “ከማር የጣፈጠ ምን ተገኝቶ? ከአንበሳስ ወዲያ ብርቱ ከየት መጥቶ!” አሉት። ሳምሶንም መልሶ፣ “በጊደሬ ባላረሳችሁ፣ እንቈቅልሼንም ባልፈታችሁ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሰባተኛው ቀን ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት የከተማው ሰዎች፥ “ከማር የጣፈጠ ምን ተገኝቶ? ከአንበሳስ ወዲያ ብርቱ ከየት መጥቶ” አሉት። ሳምሶንም መልሶ፥ “በጊደሬ ባላረሳችሁ፥ እንቈቅልሼንም ባልፈታችሁ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህ በሰባተኛው ቀን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት፥ የከተማይቱ ሰዎች “ከማር የጣፈጠ፥ ከአንበሳስ የበረታ ምን አለ?” ሲሉ የእንቆቅልሹን ፍች ነገሩት። ሶምሶንም “በእኔ ጊደር ባታርሱ ኖሮ፥ መልሱን ማግኘት ባልቻላችሁም ነበር” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በሰባተኛውም ቀን ፀሐይ ሳትገባ የከተማይቱ ሰዎች፦ ከማር የሚጣፍጥ ምንድር ነው? ከአንበሳስ የሚበረታ ማን ነው? አሉት። እርሱም፦ በጥጃዬ ባላረሳችሁ የእንቈቅልሼን ትርጓሜ ባላወቃችሁ ነበር አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 14:18
6 Referencias Cruzadas  

ሳኦ​ልና ዮና​ታን የተ​ወ​ደ​ዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውና በሞ​ታ​ቸው አል​ተ​ለ​ያ​ዩም፤ ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ ከአ​ን​በ​ሳም ይልቅ ብር​ቱ​ዎች ነበሩ።


የፊ​ታ​ቸው አም​ሳያ እን​ደ​ዚህ ነው፦ ለአ​ራቱ ሁሉ በቀ​ኛ​ቸው የሰው ፊትና የአ​ን​በሳ ፊት አላ​ቸው፤ ለአ​ራ​ቱም ሁሉ በግ​ራ​ቸው የእ​ን​ስሳ ፊትና የን​ስር ፊት አላ​ቸው።


ሰባ​ቱ​ንም የበ​ዓል ቀን አለ​ቀ​ሰ​ች​በት፤ እር​ስ​ዋም ነዝ​ን​ዛ​ዋ​ለ​ችና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ነገ​ራት። ለሕ​ዝ​ብ​ዋም ልጆች ነገ​ረ​ቻ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስ​ቀ​ሎ​ናም ወረደ፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ገፍፎ እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን ለነ​ገ​ሩት ሰዎች ሰጠ። ሶም​ሶ​ንም ተቈጣ፤ ወደ አባ​ቱም ቤት ተመ​ለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos