Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 22:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በዓ​ለቱ ቋጥኝ ላይ ለራ​ስህ መዝ​ገ​ብን ታኖ​ራ​ለህ። የሶ​ፎ​ርም ወርቅ እንደ ጅረት ድን​ጋይ ይሆ​ን​ል​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የወርቅህን አንኳር ትቢያ ላይ፣ የኦፊር ወርቅህንም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ ብትጥለው፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ወርቅን በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ወርቅን ወደ ትቢያ ጣለው፤ የኦፊርንም ወርቅ እንደ ጅረት ድንጋይ ወርውረው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የወርቅን ዕቃ በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 22:24
14 Referencias Cruzadas  

አፌ​ር​ንም፥ ኤው​ላ​ጥ​ንም፥ ዮባ​ብ​ንም ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ናቸው።


ከኦ​ፌ​ርም ወርቅ ያመ​ጣች የኪ​ራም መር​ከብ እጅግ ብዙ የተ​ጠ​ረበ እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕንቍ አመ​ጣች።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ያሠ​ራው የመ​ጠጫ ዕቃ ሁሉ ወርቅ ነበረ፤ ኵስ​ኵ​ስ​ቱም የወ​ርቅ ነበረ፤ የሊ​ባ​ኖስ ዱር የተ​ባ​ለ​ውን የዚ​ያን ቤት ዕቃ ሁሉ በወ​ርቅ አስ​ለ​በ​ጠው። የብ​ርም ዕቃ አል​ነ​በ​ረም፤ በሰ​ሎ​ሞን ዘመን የብር ዋጋ ዝቅ​ተኛ ነበ​ርና።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከ​ብን ሠራ፤ ነገር ግን መር​ከ​ቢቱ በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም።


ወደ አፌ​ርም ደረሱ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም ይዘው አገቡ።


ኦፌ​ርን፥ ሄው​ላን፥ ኦራ​ምን፥ ዑካ​ብን ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ነበሩ።


የሆ​ርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስ​ል​ኤል የሠ​ራው የናስ መሠ​ዊያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎ​ሞ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይፈ​ል​ጓት ነበር።


የኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሴ​ፌር ለሰ​ሎ​ሞን ወርቅ አመጡ፤ የሰ​ን​ደል እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕን​ቍም ደግሞ አመጡ።


ንጉ​ሡም ወር​ቁ​ንና ብሩን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ፥ የዝ​ግ​ባ​ው​ንም እን​ጨት በቆላ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ሾላ ብዛት አደ​ረ​ገው።


ሁሉን የሚ​ችል አም​ላ​ክም ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ይረ​ዳ​ሃል። ንጽ​ሕ​ና​ንም በእ​ሳት እንደ ተፈ​ተነ ብር አድ​ርጎ ይመ​ል​ስ​ል​ሃል።


“ወር​ቄን በመ​ሬት ውስጥ ቀብሬ እንደ ሆነ፥ ዋጋው ብዙ በሆነ ዕንቍ ታም​ኜም እንደ ሆነ፥


ሀብቴ በበዛ ጊዜ፥ ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፥ ስፍር ቍጥር በሌ​ለ​ውም መዝ​ገብ ላይ እጄን ጨምሬ እንደ ሆነ፥


ከም​ድር ዳርቻ ጦር​ነ​ትን ይሽ​ራል፤ ቀስ​ትን ይሰ​ብ​ራል፥ ጋሻ​ንም ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፥ በእ​ሳ​ትም የጦር መሣ​ሪ​ያን ያቃ​ጥ​ላል።


የተ​ረ​ፉ​ትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከ​በሩ ይሆ​ናሉ፤ ሰውም ከሰ​ን​ፔር ዕንቍ ይልቅ የከ​በረ ይሆ​ናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos