ሕዝቅኤል 41:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 በምዕራብም በኩል በልዩ ስፍራ አንጻር የነበረ ግቢ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግቢውም ዙሪያ የነበረ ግንብ ወርዱ አምስት ክንድ፥ ርዝመቱም ዘጠና ክንድ ነበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 በምዕራብ በኩል ከቤተ መቅደሱ ግቢ ትይዩ የሆነው ሕንጻ ወርድ ሰባ ክንድ ነበር። የሕንጻው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ርዝመቱ ዘጠና ክንድ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 በባሕር መንገድ በኩል በተለየው ስፍራ አንጻር የነበረው ሕንጻ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። የሕንጻው ግንብ ዙሪያ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱ ደግሞ ዘጠና ክንድ ነበረ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 በምዕራብ በኩል በባዶው ቦታ ጫፍ አንድ ሕንጻ አለ፤ የሕንጻው ግድግዳ ውፍረት ዙሪያው አምስት ክንድ፥ ወርዱ ሰባ ክንድ፥ ርዝመቱ ደግሞ ዘጠና ክንድ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 በምዕራብም በኩል በልዩ ስፍራ አንጻር የነበረ ግቢ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግቢውም ዙሪያ የነበረ ግንብ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱም ዘጠና ክንድ ነበረ። Ver Capítulo |