ዘፀአት 29:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 አንዱን ጠቦት በነግህ፥ ሁለተኛውንም ጠቦት በሠርክ መሥዋዕት አድርገህ ታቀርበዋለህ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም39 አንዱን ጠቦት በማለዳ፣ ሌላውን በማታ አቅርብ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 አንዱን ጠቦት ጠዋት ሁለተኛውን ጠቦት ደግሞ ማታ ታቀርበዋለህ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 ከጠቦቶቹ አንዱን ጠዋት ሌላውን ማታ ትሠዋለህ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 አንዱን ጠቦት በማለዳ ቍርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ፤ ሁለተኛውንም ጠቦት በማታ ቍርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ። Ver Capítulo |
ንጉሡም አካዝ፥ “የሚቃጠለውን የጥዋት መሥዋዕት፥ የማታውንም የእህሉን ቍርባን፥ የንጉሡንም መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሕዝቡንም ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን፥ የመጠጡንም ቍርባን በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ደም ሁሉ፥ የሌላውንም መሥዋዕታቸውን ደም ሁሉ በእርሱ ላይ ርጭበት፤ የናሱ መሠዊያ ግን በየጥዋቱ ለእኔ ይሁን” ብሎ ካህኑን ኦርያን አዘዘው።