Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 6:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሰሎ​ሞ​ንም ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መድ​ረክ ሠርቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ መካ​ከል ተክ​ሎት ነበር፤ በላ​ዩም ቆመ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ ፊት በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሰሎሞንም ርዝመቱ ዐምስት ክንድ፣ ወርዱ ዐምስት ክንድ፣ ከፍታውም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መድረክ በውጭው አደባባይ መካከል አሠርቶ ነበር፤ በመድረኩም ላይ ወጥቶ በመቆም በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ተንበርክኮ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሰሎሞንም ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መደገፊያ ሠርቶ በአደባባዩ መካከል ተክሎት ነበር፥ በእርሱም ላይ ቆመ፥ በእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ፊት በጉልበቱ ተንበርክኮ እጁን ወደ ሰማይ ዘርግቶ፥

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 6:13
14 Referencias Cruzadas  

የው​ስ​ጠ​ኛ​ው​ንም አደ​ባ​ባይ ቅጥር ሦስ​ቱን ተራ በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ፥ አን​ዱ​ንም ተራ በዝ​ግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመ​ቅ​ደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለ​ልም መጋ​ረጃ ሠራ።


በታ​ላ​ቁም አደ​ባ​ባይ ዙሪያ የነ​በ​ረው ቅጥር እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ቅጥ​ርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ አን​ዱም ወገን በዝ​ግባ ሳንቃ ተሠ​ርቶ ነበር።


ሰሎ​ሞ​ንም ይህ​ችን ጸሎ​ትና ልመና ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸልዮ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ፥ እጁ​ንም ወደ ሰማይ ዘር​ግቶ ነበ​ርና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ከሰ​ገ​ደ​በት ተነሣ።


ደግ​ሞም የካ​ህ​ና​ቱን አደ​ባ​ባይ ፥ ታላ​ቁ​ንም አደ​ባ​ባይ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጆች ሠራ፤ ደጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በናስ ለበጠ።


ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ ፊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አን​ጻር ቆሞ እጆ​ቹን ዘረጋ።


በሠ​ር​ክም መሥ​ዋ​ዕት ጊዜ ልብ​ሴና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያዬ እንደ ተቀ​ደደ ሆኖ ከመ​ዋ​ረዴ ተነ​ሣሁ፤ በጕ​ል​በ​ቴም ተን​በ​ር​ክኬ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጄን ዘረ​ጋሁ።


ይህ​ንም ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ ተቀ​ምጬ አለ​ቀ​ስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰ​ማ​ይም አም​ላክ ፊት እጾ​ምና እጸ​ልይ ነበር፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦


ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር።


እም​ነ​ትና በጎ​ነት በፊቱ፥ ቅድ​ስ​ናና የክ​ብር ገና​ና​ነት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ናቸው።


ሙሴም፥ “ለፈ​ር​ዖን ከከ​ተማ በወ​ጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐ​ድ​ጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረ​ዶ​ውም፥ ዝና​ቡም ደግሞ አይ​ወ​ር​ድም።


የድ​ን​ጋይ ውር​ወራ ያህ​ልም ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብሎ እየ​ሰ​ገደ ጸለየ።


ይህ​ንም ከአለ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ አብ​ረ​ውት ካሉት ሁሉ ጋር ጸለየ።


ከዚ​ህም በኋላ ለመ​ሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር እስከ ከተ​ማው ውጭ ሸኙን፤ በባ​ሕ​ሩም ዳር ተን​በ​ር​ክ​ከን ጸለ​ይን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos