Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 36:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በኤ​ር​ም​ያ​ስም አፍ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ር​ስን ንጉሥ የቂ​ሮ​ስን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ሁሉ አዋጅ ይነ​ገር ዘንድ በጽ​ሕ​ፈት እን​ዲህ ሲል አዘዘ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ ዘመነ መንግሥት በመጀመሪያ ዓመት፣ በኤርምያስ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በግዛቱ ሁሉ ዐዋጅ እንዲያስነግርና ይህም እንዲጻፍ እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሣሣ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በኤርምያስም አንደበት የተነገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ ነገረ፥ ደግሞም በጽሑፍ እንዲህ ብሎ አወጀ፦

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ አማካይነት አስቀድሞ የተናገረው የትንቢት ቃል፥ ቂሮስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በመጀመሪያው ዓመት ተፈጸመ፤ ከዚህ የሚከተለውን ዐዋጅ እንዲያወጣና በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ሁሉ በጽሑፍ በማስተላለፍ ከፍ ባለ ድምፅ ለሕዝቡ በንባብ እንዲገለጥ ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር ቂሮስን አነሣሣው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በኤርምያስም አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 36:22
24 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርን ከረ​ም​ማ​ቴር ወገን የኤ​ል​ያ​ዳሔ ልጅ ኤስ​ሮ​ምን የሲባ ንጉሥ ጌታ​ውን አድ​ረ​ዓ​ዛ​ርን ጠላት አድ​ርጎ በሰ​ሎ​ሞን ላይ አስ​ነሣ። ሰዎ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ። የዓ​መ​ፁም አበ​ጋዝ እርሱ ነበር። ደማ​ስ​ቆ​ንም እጅ አደ​ረ​ጋት። በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠላት ሆነ። ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርም ከኤ​ዶ​ም​ያስ ነገ​ሥ​ታት ዘር ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከጌ​ታው ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር የኰ​በ​ለ​ለ​ውን የኤ​ል​ያ​ዳን ልጅ ሬዞ​ንን ጠላት አድ​ርጎ አስ​ነ​ሣ​በት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያን አጠ​ገብ የሚ​ኖ​ሩ​ትን የዓ​ረ​ብ​ያን ሰዎች በኢ​ዮ​ራም ላይ አስ​ነሣ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ ሙሴ በም​ድረ በዳ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያዘ​ዘ​ውን ግብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመጡ ዘንድ፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ አዘዘ።


እንደ ተጻ​ፈም ብዙ​ዎቹ አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​መጡ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ አዋጅ እን​ዲ​ነ​ገር ወሰኑ።


በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲ​ፈ​ጸም፥ ምድ​ሪቱ ሰን​በ​ትን በማ​ድ​ረ​ግዋ እስ​ክ​ታ​ርፍ ድረስ፥ በተ​ፈ​ታ​ች​በ​ትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ሰን​በ​ትን አገ​ኘች።


“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ እር​ሱም በይ​ሁዳ ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ አዝ​ዞ​ኛል፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ እር​ሱም ይውጣ።”


የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት ይወጡ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሳ​ቸ​ውን ያነ​ሣ​ሣው ሁሉ ተነሡ።


ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።


እኔ ቂሮ​ስን በጽ​ድቅ አስ​ነ​ሥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ አቀ​ና​ለሁ፤ እርሱ ከተ​ማ​ዬን ይሠ​ራል፤ በዋ​ጋም ወይም በጉቦ ሳይ​ሆን ምር​ኮ​ኞ​ችን ያወ​ጣል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


“ሰባው ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት እነ​ር​ሱን ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ እኔም እንደ አደ​ራ​ረ​ጋ​ቸ​ውና እንደ እጃ​ቸው ሥራ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰባው ዓመት በባ​ቢ​ሎን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ እጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ለሁ፥ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ችሁ ዘንድ መል​ካ​ሚ​ቱን ቃሌን እፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እግዚአብሔርም የይሁዳን አለቃ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁንም ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፣ በንጉሡም በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን መጡ፥ የአምላካቸውንም የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት ሠሩ።


እን​ግ​ዲህ የማ​ይ​ና​ወ​ጠ​ውን የተ​ስ​ፋ​ች​ንን እም​ነት እና​ጽና፤ ተስፋ የሰጠ እርሱ የታ​መነ ነውና።


አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ላይ አስ​ነ​ሥ​ቶህ እን​ደ​ሆነ፥ ቍር​ባ​ን​ህን ይቀ​በል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አም​ልክ ብለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ላይ እን​ዳ​ል​ቀ​መጥ ዛሬ ጥለ​ው​ኛ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉ​ማን ይሁኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos