Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 29:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ካህ​ና​ቱም ያነ​ጹት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስጥ ገቡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መቅ​ደስ ያገ​ኙ​ትን ርኩስ ነገር ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ አወ​ጡት። ሌዋ​ው​ያ​ንም ወስ​ደው ወደ ሜዳ ወደ ቄድ​ሮን ወንዝ ጣሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ካህናቱ የእግዚአብሔርን መቅደስ ለማንጻት ወደ ውስጡ ገቡ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ያገኙትንም ማንኛውንም የረከሰ ነገር ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ አወጡት። ሌዋውያኑም ተሸክመው በመውሰድ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ ጣሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ካህናቱም መቅደሱን ለማንጻት ወደ ጌታ ቤት ወደ ውስጡ ገቡ፥ በጌታም መቅደስ ያገኙትን ርኩስ ነገር ሁሉ ወደ ጌታ ቤት አደባባይ አወጡት። ሌዋውያንም ወስደው ወደ ሜዳ ወደ ቄድሮን ወንዝ ጣሉት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ካህናቱም ቤተ መቅደሱን ለማንጻት ወደ ውስጡ ገቡ፤ ያልነጻውንም ነገር ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ አወጡት፤ ሌዋውያኑም ከዚያ አንሥተው ከከተማ ውጪ በመውሰድ በቄድሮን ሸለቆ ጣሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ካህናቱም ያነጹት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጡ ገቡ፤ በእግዚአብሔርም መቅደስ ያገኙትን ርኩስ ነገር ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት አደባባይ አወጡት። ሌዋውያንም ወስደው ወደ ሜዳ ወደ ቄድሮን ወንዝ ጣሉት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 29:16
15 Referencias Cruzadas  

ሀገ​ሪ​ቱም ሁላ በታ​ላቅ ድምፅ አለ​ቀ​ሰች። ሕዝ​ቡም ሁሉ በቄ​ድ​ሮን ወንዝ ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ደግሞ የቄ​ድ​ሮ​ንን ወንዝ ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡና ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተሻ​ገሩ።


ንጉ​ሡም አሳ እና​ቱን መዓ​ካን ለአ​ስ​ጣ​ር​ቴስ ስለ ሰገ​ደች ከእ​ቴ​ጌ​ነቷ አወ​ረ​ዳት፤ አሳም ምስ​ሉን ቈርጦ ቀጠ​ቀ​ጠው፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ወንዝ አጠ​ገብ አቃ​ጠ​ለው።


ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑ​ንም ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ ስድ​ስት መቶ መክ​ሊት በሚ​ያ​ህል በጥሩ ወር​ቅም ኪሩ​ቤ​ልን ለበ​ጣ​ቸው።


ተነ​ሥ​ተ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችና ለጣ​ዖ​ታት የሚ​ያ​ጥ​ኑ​በ​ትን ዕቃ ሁሉ አስ​ወ​ገዱ፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ወንዝ ጣሉት።


ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤትዋ አም​ጥ​ተው በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች በነ​በ​ረው መቅ​ደስ አኖ​ሯት።


ዕቃ ቤቶ​ቹ​ንም እን​ዲ​ያ​ነጹ አዘ​ዝሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ​ዎች፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ ዕጣ​ኑ​ንም መልሼ በዚያ አገ​ባሁ።


ከር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እህ​ል​ንም እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ው​ማ​ለሁ፤ ራብ​ንም አላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ተና​ግሮ አት​ክ​ልት ወደ አለ​በት ስፍራ ወደ ቄድ​ሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወጣ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጋር ወደ​ዚያ ገባ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos