Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 20:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጠላ​ቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ሀት ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንዴት እንደ ተዋጋቸው በሰሙ መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርሀት ወደቀባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጌታ የእስራኤልን ጠላቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ የጌታር ፍርሃት አደረባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንዴት እንደ ተዋጋ የሰሙ መንግሥታት ሁሉ የእግዚአብሔር ፍርሀትና ድንጋጤ ዐደረባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ፍርሃት ሆነ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 20:29
14 Referencias Cruzadas  

እስ​ራ​ኤ​ልም ከሴ​ቄም ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት በዙ​ሪ​ያ​ቸው ባሉት ከተ​ሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ለማ​ሳ​ደድ አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሶ​ር​ያ​ው​ያን የሰ​ረ​ገላ ድምፅ፥ የፈ​ረስ ድም​ፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰ​ምቶአ​ቸ​ዋ​ልና፥ እርስ በር​ሳ​ቸው “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ይከ​ቡን ዘንድ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንና የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ነገ​ሥት ቀጥሮ አም​ጥ​ቶ​ብ​ናል” ይባ​ባሉ ነበር።


አሳም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌዶር ሀገር ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንም ፈጽ​መው እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ ወደቁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ተሰ​ባ​ብ​ረ​ዋ​ልና፤ እጅ​ግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ታላቅ ድን​ጋጤ ስለ ወደ​ቀ​ባ​ቸው በጌ​ዶር ዙሪያ የነ​በ​ሩ​ትን ከተ​ሞች ሁሉ መቱ፤ በከ​ተ​ሞ​ቹም ውስጥ እጅግ ብዙ ምር​ኮና ብዝ​በዛ ነበ​ርና ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ማረኩ።


በይ​ሁ​ዳም ዙሪያ በነ​በሩ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ድን​ጋጤ ሆነ፤ ከኢ​ዮ​ሳ​ፍ​ጥም ጋር አል​ተ​ዋ​ጉም።


በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገቡ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምስ ምሕ​ረ​ቱን ለልጅ ልጅ ይቈ​ር​ጣ​ልን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እና​ንተ ይዋ​ጋል፤ እና​ን​ተም ዝም ትላ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም መን​ኰ​ራ​ኵር አሰረ፤ ወደ ጭን​ቅም አገ​ባ​ቸው፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ይዋ​ጋ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እን​ሽሽ” አሉ።


በፊ​ትህ መፈ​ራ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን ሕዝብ ሁሉ አስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ እን​ዲ​ሸ​ሹ​ልህ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል የነ​በ​ሩት የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሩም አጠ​ገብ የነ​በሩ የፊ​ኒ​ቃ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባ​ቸው ቀለጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ሳቱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos