Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ ከቀ​ዓት ልጆ​ችና ከቆሬ ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከፍ ባለ ታላቅ ድምፅ ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከቀዓትና ከቆሬ ወገኖች ጥቂት ሌዋውያንም ቆመው፣ እጅግ ከፍ ባለ ድምፅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሌዋውያንም፥ የቀዓት ልጆችና የቆሬ ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ ጌታን እጅግ ታላቅ በሆነ ድምፅ ሊያመሰግኑት ቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የቀዓትና የቆሬ ጐሣዎች አባላት የሆኑ ሌዋውያን ቆሙ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሌዋውያንም፥ የቀዓት ልጆችና የቆሬ ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በእጅግ ታላቅ ድምጽ ያመሰገኑት ዘንድ ቆሙ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 20:19
16 Referencias Cruzadas  

ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ካህ​ናቱ ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ሰ​ማት መለ​ከ​ትና ጸና​ጽል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መዝ​ሙ​ራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤ​ዶ​ታም ልጆች ግን በረ​ኞች ነበሩ።


አለ​ቃ​ውም አሳፍ ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም ቀጥሎ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ሔል፥ ሰሜ​ራ​ሞት፥ ይሔ​ኤል፥ ማታ​ትያ፥ ኤል​ያብ፥ በና​ያስ፥ አብ​ዲ​ዶም፥ ይዒ​ኤል በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ አሳ​ፍም በጸ​ና​ጽል ይዘ​ምሩ ነበር።


አራቱ ሺህም በረ​ኞች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለም​ስ​ጋና በተ​ሠ​ሩት በዜማ ዕቃ​ዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በም​ድር ላይ ሰገደ፤ ይሁ​ዳም ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደቁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገዱ።


ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁ​ሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወ​ጡም ኢዮ​ሣ​ፍጥ ቆመና፥ “ይሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፥ ትጸ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ፤ በነ​ቢ​ዩም እመኑ፤ ነገ​ሩም ይቀ​ና​ላ​ች​ኋል” አለ።


መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ መዘ​ም​ራኑ በአ​ን​ድ​ነት ሆነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” እያሉ በአ​ንድ ቃል ድም​ፃ​ቸ​ውን ወደ ላይ ከፍ አድ​ር​ገው በመ​ለ​ከ​ትና በጸ​ና​ጽል፥ በዜ​ማም ዕቃ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባመ​ሰ​ገኑ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ብሩ ደመና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች፥ የሰ​ራ​ብያ ልጅ ሴኬ​ንያ፥ የከ​ናኒ ልጆ​ችም በደ​ረ​ጃ​ዎች ላይ ቆመው ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በታ​ላቅ ድምፅ ጮኹ።


ልቤ መል​ካም ነገ​ርን ተና​ገረ፥ እኔም ሥራ​ዬን ለን​ጉሥ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አን​ደ​በቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።


የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፥ ምድ​ር​ንም ጠራት፤ ከፀ​ሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግ​ቢ​ያዋ ድረስ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ማ​ል​ክት ማኅ​በር ቆመ፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል።


የቆሬ ልጆች አሴር፥ ሕል​ቃና፥ አብ​ያ​ሳፍ ናቸው፤ እነ​ዚህ የቆሬ ልጆች ትው​ልድ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos