1 ዜና መዋዕል 28:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለመቅደስ የሚሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መርጦሃልና ጠንክረህ ፈጽመው።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ለመቅደስ የሚሆን ቤት እንድትሠራ እግዚአብሔር የመረጠህ መሆኑን አሁንም ዐስብ፤ በርትተህም ሥራ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አሁንም፥ እነሆ፥ ጌታ ለመቅደስ የሚሆን ቤትን እንድትሠራ መርጦሃልና በርትተህ በቈራጥነት ፈጽመው።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ቤተ መቅደሱን ትሠራለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን እንደ መረጠህ አትዘንጋ፤ አሁንም በርትተህ በቈራጥነት ሥራው።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለመቅደስ የሚሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መርጦሃልና ጠንክረህ ፈጽመው።” Ver Capítulo |
ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን፥ “ጠንክር፤ ሰው ሁን፤ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነውን ሥራ ሁሉ እስክትፈጽም ድረስ እርሱ አይተውህም፤ አይጥልህምም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአደባባዩ፥ የቤተ መዛግብቱ፥ የሰገነቱ፥ የውስጡ ቤተ መዛግብት፥ የስርየት ቤቱና፥ የእግዚአብሔር ቤት ምሳሌ።