Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 14:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የጢ​ሮ​ስም ንጉሥ ኪራም ቤት ይሠ​ሩ​ለት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም ወደ ዳዊት ላከ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን ከዝግባ ዕንጨት ጋራ ላከ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤት እንዲሠሩለት መልእክተኞችን የዝግባ እንጨትንም ጠራቢዎችንም አናጢዎችንም ወደ ዳዊት ላከ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ፤ ከእነርሱም ጋር ለዳዊት ቤተ መንግሥት የሚሠሩለት የሊባኖስ ዛፍ ግንድ የያዙ አናጢዎችና ግንበኞች ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ቤት ይሠሩለት ዘንድ መልእክተኞችን የዝግባ እንጨትንም ጠራቢዎችንም አናጢዎችንም ወደ ዳዊት ላከ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 14:1
16 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እኔ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጬ​አ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ግን በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።


የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በዘ​መኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎ​ሞን በአ​ባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመ​ሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ወደ ሰሎ​ሞን ላከ።


ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ሰባ ሺህ ተሸ​ካ​ሚ​ዎች፥ ሰማ​ንያ ሺህም በተ​ራ​ራው ላይ ድን​ጋይ የሚ​ጠ​ርቡ ጠራ​ቢ​ዎች ነበ​ሩት።


የሰ​ሎ​ሞ​ንና የኪ​ራም አና​ጢ​ዎች፥ ጌባ​ላ​ው​ያ​ንም ወቀ​ሩ​አ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ረ​ትም አኖ​ሩ​አ​ቸው፤ ቤቱ​ንም ለመ​ሥ​ራት እን​ጨ​ቱ​ንና ድን​ጋ​ዮ​ቹን ሦስት ዓመት አዘ​ጋጁ።


አሁ​ንም ከወ​ገኔ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያን እን​ጨት መቍ​ረጥ የሚ​ያ​ውቅ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ለ​ህና የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ ይቈ​ር​ጡ​ልኝ ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን እዘዝ፤ አገ​ል​ጋ​ዮቼም ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ይሁኑ፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ዋጋ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ሁሉ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


ስለ ሕዝ​ቡም ስለ እስ​ራ​ኤል፥ መን​ግ​ሥቱ እጅግ ከፍ ብሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጀው ዳዊት ዐወቀ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እነሆ፥ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጫ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ግን በመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎች ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።


ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር የነ​በ​ሩ​ትን መጻ​ተ​ኞች ይሰ​በ​ስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ለመ​ሥ​ራት የሚ​ወ​ቀ​ሩ​ትን ድን​ጋ​ዮች ይወ​ቅሩ ዘንድ ጠራ​ቢ​ዎ​ችን አኖረ።


ሰሎ​ሞ​ንም የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሰባ ሺህ፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ድን​ጋ​ዮ​ችን የሚ​ጠ​ር​ቡ​ትን ሰማ​ንያ ሺህ፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ሦስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ሰዎች ሰበ​ሰበ።


ሰሎ​ሞ​ንም እን​ዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ቤት ይሠራ ዘንድ የዝ​ግባ እን​ጨት እንደ ላክ​ህ​ለት፥ እን​ዲሁ ለእኔ አድ​ርግ።


ለጠ​ራ​ቢ​ዎ​ችና ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችም ብር ሰጡ፤ የፋ​ር​ስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀ​ደ​ላ​ቸው የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ በባ​ሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲ​ዶ​ናና ለጢ​ሮስ ሰዎች መብ​ልና መጠጥ፥ ዘይ​ትም ሰጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos