Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 7:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንዲት ያገባች ሴት ከባሏ ጋራ በሕግ የታሰረች የምትሆነው እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ነው፤ ባሏ ቢሞት ግን ከጋብቻ ሕግ ነጻ ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ በሕግ ታስራለችና፤ ባሏ ቢሞት ግን ከባል ሕግ ተፈትታለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ለምሳሌ፥ ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ ከእርሱ ጋር በሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ከሞተ ግን ከታሰረችበት ሕግ ነጻ ናት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ከእ​ርሱ ጋር በሕግ የታ​ሰ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚ​ስ​ት​ነት ታስ​ራ​በት ከኖ​ረ​ችው ሕግ የተ​ፈ​ታች ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 7:2
6 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ሰው ብታገባ አመንዝራ ትባላለች፤ ባሏ ቢሞት ግን ሌላ ሰው ብታገባም እንኳ፣ ከዚያ ሕግ ነጻ ትሆናለች፤ አመንዝራ አትባልም።


አሁን ግን ቀድሞ ጠፍሮ አስሮን ለነበረው ሞተን፣ ከሕግ ነጻ ወጥተናል፤ ይህም አሮጌ በሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ አዲስ በሆነው በመንፈስ መንገድ እንድናገለግል ነው።


አንዲት ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ከርሱ ጋራ የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን፣ የፈለገችውን ሰው ለማግባት ነጻነት አላት፤ ሰውየው ግን በጌታ መሆን አለበት።


ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም፤ ባሏ እንጂ። እንዲሁም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሚስቱ እንጂ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos