16 በሥርዐትህ ደስ ይለኛል፤ ቃልህንም አልዘነጋም።
16 በድንጋጌዎችህ ደስ ይለኛል፥ ቃልህንም አልረሳም።
16 በሕግህ ደስ ይለኛል፤ ቃልህንም አልረሳም።
ነገር ግን ደስ የሚሠኘው በእግዚአብሔር ሕግ ነው፤ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል።
ነፍሴ ዘወትር አደጋ ላይ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
አንተን እንዳልበድል፣ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
ሰው በሀብቱ ብዛት ደስ እንደሚለው፣ ምስክርነትህን በመከተል ደስ ይለኛል።
እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ፤ ነገር ግን መመሪያህን አልዘነጋሁም።
መከራና ሥቃይ ደርሶብኛል፤ ነገር ግን ትእዛዝህ ደስታዬ ነው።
ሕግህን አልረሳሁምና፣ ሥቃዬን ተመልከት፤ ታደገኝም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ ሕግህም ደስታዬ ነው።
እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ ትእዛዞችህን አልረሳሁምና፣ ባሪያህን ፈልገው።
ምስክርነትህ ለእኔ ደስታዬ ነው፤ መካሪዬም ነው።
በርሷ ደስ ይለኛልና፣ በትእዛዝህ መንገድ ምራኝ።
እኔ እወድደዋለሁና፣ በትእዛዝህ ደስ ይለኛል።
የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ፤ እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም።
ልባቸው የሠባና የደነደነ ነው፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል።
ሕግህ ደስታዬ ነውና፣ በሕይወት እኖር ዘንድ ቸርነትህ ትምጣልኝ።
ጢስ የጠጣ የወይን አቍማዳ ብመስልም፣ ሥርዐትህን አልረሳሁም።
አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።”
ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሠኘዋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።
ልጄ ሆይ፤ ትምህርቴን አትርሳ፤ ትእዛዞቼን በልብህ ጠብቅ፤
ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።
በውስጤ በእግዚአብሔር ሕግ ሐሤት አደርጋለሁ፤