Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 18:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፥ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አንደበትህ ሕይወትህን ሊያድን ወይም ሊያጠፋ ይችላል፤ ስለዚህ በአንደበትህ ወዳጆችን ብታፈራ ተደስተህ ትኖራለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 18:21
21 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣ ስለ ድኾችም ጩኸት፣ አሁን እነሣለሁ፤ በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል።


የጻድቃን አንደበት ጥበብን ያፈልቃል፤ ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች።


የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፤ ነፍሳትን የሚማርክም ጠቢብ ነው።


ክፉ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፤ ጻድቅ ሰው ግን ከመከራ ያመልጣል።


አንደበቱንና ምላሱን የሚቈጣጠር፣ ራሱን ከመቅሠፍት ይጠብቃል።


ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገሯቸው፤ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና።


በእስራኤል አልቃሾች ከንፈር ላይ ምስጋና እፈጥራለሁ። በቅርብና በሩቅ ላሉት ሰላም፣ ሰላም ይሁን፤ እኔ እፈውሳቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።


እናንተ ግን ክፋትን ዘራችሁ፤ ኀጢአትንም ዐጨዳችሁ፤ የሐሰትንም ፍሬ በላችሁ። በራሳችሁ ጕልበት፣ በተዋጊዎቻችሁም ብዛት ታምናችኋልና፣


እንግዲህ የርሱ አገልጋዮች፣ የጽድቅ አገልጋዮች ለመምሰል ራሳቸውን ቢለውጡ የሚያስገርም አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።


ለሚጠፉት ወደ ሞት የሚወስድ የሞት ሽታ፣ ለሚድኑት ግን ወደ ሕይወት የሚወስድ የሕይወት ሽታ ነን፤ ታዲያ፣ ለዚህ ብቁ የሚሆን ማን ነው?


እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ።


ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ በጨው እንደ ተቀመመ ሁልጊዜ በጸጋ የተሞላ ይሁን።


ከንቱ ቃል እየደረደሩ በስሕተት ከሚኖሩት መካከል አምልጠው የመጡትን ሰዎች በሴሰኛ ሥጋዊ ምኞት በማባበል ያታልላሉና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos