Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሰቈቃወ 2:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ እንደ ቈሰሉ ሰዎች ሲደክሙ፣ በእናታቸው ክንድ ላይ፣ ነፍሳቸው በመውጣት ላይ ሳለች፣ “ምግብና የወይን ጠጅ የት አለ?” እያሉ እናቶቻቸውን ይጠይቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ላሜድ። በከተማ ጐዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍሳቸውም በእናቶቻቸው ብብት በወጣች ጊዜ፥ እናቶቻቸውን፦ እህልና የወይን ጠጅ ወዴት አለ? ይሉአቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በጦር ሜዳ እንደ ቈሰለ ወታደር በከተማው መንገዶች እየተዝለፈለፉ በእናታቸው ክንድ ላይ ሆነው፥ “ምግብና ውሃ!” እያሉ እያለቀሱ፥ ሕይወታቸው ያልፋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ላሜድ። በከ​ተማ ጎዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በእ​ና​ቶ​ቻ​ቸው ብብት እለይ-እለይ ባለች ጊዜ፥ እና​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ “እህ​ልና ወይን ወዴት አለ?” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ላሜድ። በከተማ ጐዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍሳቸውም በእናቶቻቸው ብብት በወጣች ጊዜ፥ እናቶቻቸውን፦ እህልና የወይን ጠጅ ወዴት አለ? ይሉአቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 2:12
9 Referencias Cruzadas  

“አሁን ነፍሴ በውስጤ ዐለቀች፤ የመከራ ዘመንም ይዞኛል።


ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች፣ እነዚህን ነገሮች አስታወስሁኝ፤ ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ፣ በእልልታና በምስጋና መዝሙር፣ በአእላፍ ሕዝብ መካከል፣ እንዴት ከሕዝቡ ጋራ እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ።


ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በርሱ ታመኑ፤ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ


ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ፣ በየጐዳናው አደባባይ ላይ ተኝተዋል። የእግዚአብሔር ቍጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሞልቶባቸዋል።


ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች ጋራ እሰጠዋለሁ፤ ምርኮውን ከኀያላን ጋራ ይካፈላል፤ እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣ ከክፉ አድራጊዎችም ጋራ በመቈጠሩ፣ የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።


ሰብልህንና ምግብህን ጠራርገው ይበሉብሃል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይውጣሉ፤ በጎችህንና ከብቶችህን ይፈጃሉ፤ የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ያወድማሉ፤ የታመንህባቸውንም የተመሸጉ ከተሞች በሰይፍ ያጠፏቸዋል።


እንጀራ በመፈለግ፣ ሕዝቧ ሁሉ በሥቃይ ይጮኻል፤ በሕይወት ለመኖር፣ የከበረ ሀብታቸውን በምግብ ይለውጣሉ፤ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ ተመልከተኝም፤ እኔ ተዋርጃለሁና።”


ከውሃ ጥም የተነሣ፣ የሕፃናት ምላስ ከላንቃቸው ጋራ ተጣበቀ፤ ልጆቹ ምግብ ለመኑ፤ ነገር ግን ማንም አልሰጣቸውም።


የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos