Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 33:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሐሤትና የደስታ ድምፅ፣ የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ እንዲሁም፣ “ ‘ “እግዚአብሔር ቸር ነውና፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤” የሚል የምስጋናን መሥዋዕት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጡ ሰዎች ድምፅ ይሰማል፤ የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ እመልሳለሁና፤’ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሐ​ሤት ድም​ፅና የደ​ስታ ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽራ ድም​ፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​መጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰ​ማል። የዚ​ያ​ችን ምድር ምር​ኮ​ኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡት ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የምድርን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 33:11
47 Referencias Cruzadas  

ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።


እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አሳውቁ።


ከሕዝቡም ጋራ ከተመካከረ በኋላ ከሰራዊቱ ፊት ቀድመው በመሄድ፣ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” እያሉ ለእግዚአብሔር የሚዘምሩና ስለ ቅድስናውም ክብር የሚያወድሱ ሰዎችን መደበ።


ከዚያም ሕዝቅያስ፣ “እነሆ፤ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችኋል፤ አሁንም ቅረቡ፤ መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አምጡ” አላቸው። ስለዚህ ጉባኤው መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ አመጡ፤ ልባቸው የፈቀደ ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።


መለከት ነፊዎችና ዘማሪዎችም በአንድነት አንድ ድምፅ ሆነው ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና አቀረቡ፤ በመለከት፣ በጸናጽልና በሌሎች መሣሪያዎች ታጅበውም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔርን እያወደሱ፣ “እርሱ ቸር ነው፣ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉ ዘመሩ። ከዚያም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በደመና ተሞላ።


እስራኤላውያንም ሁሉ እሳቱ ሲወርድ፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ከቤተ መቅደሱ በላይ ሲያዩ፣ በመተላለፊያው ወለል ላይ ተንበረከኩ፤ በግንባራቸውም ወደ መሬት ተደፍተው ሰገዱ፤ እንዲህ እያሉም ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረቡ፤ “እርሱ ቸር ነውና፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


እግዚአብሔር ደስ እንዲሰኙ ስላደረጋቸው የቂጣን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አከበሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ልብ ለውጦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ቤት ሥራ እንዲያግዛቸው አድርጎ ነበር።


እግዚአብሔር ታላቅ ደስታ ስለ ሰጣቸው፣ በዚያች ዕለት ደስ ብሏቸው ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሴቶችና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም የነበረው የደስታ ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር።


ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ የተነገራቸውን ቃል ተረድተው ስለ ነበረ፣ ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ከምግባቸው ከፍለው ለመላክና ሐሤትም ለማድረግ ሄዱ።


ሃሌ ሉያ። ቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።


ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና።


የምስጋናም መሥዋዕት ያቅርቡለት፤ ሥራውንም ደስ በሚል ዝማሬ ይግለጹ።


ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።


እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኳል።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ ማዳንህን ለግሰን።


እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።


እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።


እግዚአብሔር ጽዮንን በርግጥ ያጽናናታል፤ ፍርስራሾቿንም በርኅራኄ ይመለከታል፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔድን፣ በረሓዋንም እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፤ ተድላና ደስታ፣ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ በርሷ ይገኛሉ።


ስሚ! ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገዋል፤ በአንድነት በእልልታ ይዘምራሉ። እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ፣ በዐይኖቻቸው ያያሉ።


እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቷል፤ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷልና።


የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ፤ በዐይናችሁ ፊት፣ በዘመናችሁም የደስታና የሐሤት ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስወግዳለሁ።’


ሰዎች ከይሁዳ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ ከብንያምም አገር፣ ከቈላውና ከደጋው አገር እንዲሁም ከኔጌብ የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ።


የደስታንና የእልልታን ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ፣ የወፍጮን ድምፅና የመብራትን ብርሃን አስቀራለሁ።


እኔም እገኝላችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከምርኮም እመልሳችኋለሁ፤ እናንተንም ከበተንሁበት አገርና ስፍራ ሁሉ እመልሳችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምርኮ ምክንያት ወዳስለቀቅኋችሁም ምድር እመልሳችኋለሁ።”


ከእነርሱም የምስጋና መዝሙር፣ የእልልታ ድምፅ ይሰማል። እኔ አበዛቸዋለሁ፤ ቍጥራቸውም አይቀንስም፣ አከብራቸዋለሁ፤ የተናቁም አይሆኑም።


እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቧል፤ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”


ምርኳቸውን ስለምመልስላቸው በብንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች፣ በይሁዳ ከተሞችና በተራራማው አገር ከተሞች፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች፣ መሬት በጥሬ ብር ይገዛል፤ ውሉም ተፈርሞ፤ በምስክሮች ፊት ይታሸጋል፤’ ይላል እግዚአብሔር።”


የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፤ ከልጆቹም በአብርሃም፣ በይሥሐቅና በያዕቆብ ዘር ላይ ገዥ እንዲሆኑ አልመርጥም፤ ይህንም የምለው ምርኳቸውን ስለምመልስና ስለምራራላቸው ነው።’ ”


የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ቀድሞ እንደ ነበሩት ሁኔታ አድርጌ አበጃቸዋለሁ፤


የደስታና የተድላን ድምፅ፣ የሙሽራና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም መንገዶች አጠፋለሁ፤ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለችና።


የተሰደደውን ሕዝቤን እስራኤልን እመልሳለሁ። “እነርሱም የፈራረሱትን ከተሞች መልሰው ሠርተው በውስጣቸው ይኖራሉ። የወይን ተክል ተክለው፣ ጠጁን ይጠጣሉ፤ አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።


እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ ‘ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።’ ”


እግዚአብሔር መልካም ነው፤ በጭንቅ ጊዜም መሸሸጊያ ነው። ለሚታመኑበት ይጠነቀቅላቸዋል፤


የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፤ እልል በዪ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ።


ኤፍሬማውያን እንደ ኀያላን ሰዎች ይሆናሉ፤ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ሐሤት ያደርጋል። ልጆቻቸው ያዩታል፤ ደስተኛም ይሆናሉ፤ ልባቸውም በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአራተኛው፣ የአምስተኛው፣ የሰባተኛውና የዐሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”


እንዴት ውብና አስደናቂ ይሆናሉ፤ እህል ጕልማሶችን፣ አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅትን ያሳምራል።


ሙሽራዪቱ የሙሽራው ናት፤ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን፣ የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሟል።


ስለዚህ ዘወትር የምስጋናን መሥዋዕት፣ ይኸውም ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በኢየሱስ አማካይነት ለእግዚአብሔር እናቅርብ።


የመብራት ብርሃን፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ በአስማትሽም ሕዝቦች ሁሉ ስተዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos