Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 23:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እኔ እነዚህን ነቢያት አልላክኋቸውም፤ እነርሱ ግን ለራሳቸው መልእክታቸውን ይዘው ሮጡ፣ ሳልናገራቸውም፣ ትንቢት ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እኔ ሳልልካቸው እነዚህ ነቢያት ሮጡ፤ እኔም ሳልነግራቸው ትንቢትን ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በራሳቸው ፈቃድ ፈጥነው ሄዱ እንጂ እኔ እነዚህን ነቢያት አላክኋቸውም፤ እኔ ምንም የትንቢት ቃል አልሰጠኋቸውም፤ እነርሱ ግን በስሜ ትንቢት ይናገራሉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “እኔ ሳል​ል​ካ​ቸው እነ​ዚህ ነቢ​ያት ሮጡ፤ እኔም ሳል​ነ​ግ​ራ​ቸው ትን​ቢ​ትን ተና​ገሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እኔ ሳልልካቸው እነዚህ ነቢያት ሮጡ፥ እኔም ሳልነግራቸው ትንቢትን ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 23:21
12 Referencias Cruzadas  

ከዚያም የጌታ ድምፅ፣ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁት። እኔም፣ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ!” አልሁ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውምም። የሐሰት ራእይ፣ ሟርት፣ ከንቱ ነገርንና የልባቸውን ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።


“እነሆ፤ ሐሰተኛ ሕልም ተመርኵዘው ትንቢት የሚናገሩትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “እኔ ሳልልካቸው ወይም ሳልሾማቸው ደፍረው ውሸት ይናገራሉ፤ ሕዝቤንም ያስታሉ፤ ለዚህም ሕዝብ አንዳች አይረቡትም” ይላል እግዚአብሔር።


ሐሰተኛ ትንቢት ስለሚነግሯችሁ፣ ‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሙ፤


‘እኔ አልላክኋቸውም’ ይላል እግዚአብሔር ‘የሐሰት ትንቢት በስሜ ይናገራሉ፤ ስለዚህ እናንተንና ትንቢት የሚናገሩላችሁን ነቢያት አሳድዳለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’ ”


ነቢዩ ኤርምያስም ለነቢዩ ሐናንያ እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፤ ስማ! እግዚአብሔር ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል፤


“ይህን መልእክት በምርኮ ላሉት ሁሉ እንዲህ ብለህ ላክ፤ ‘ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችሁ፣ በሐሰት እንድትታመኑ አድርጓችኋልና፣


የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በርግጥ እንዲህ ይላልና፤ “በመካከላችሁ ያሉት ነቢያትና ጠንቋዮች አያታልሏችሁ፤ የሚያልሙላችሁንም ሕልም አትስሙ፤


በስሜ ሐሰተኛ ትንቢት ይነግሯችኋል እንጂ እኔ አልላክኋቸውም” ይላል እግዚአብሔር።


ኢየሱስም እንደ ገና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን! አብ እኔን እንደ ላከኝ፣ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው።


በርናባስና ሳውልም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄዱ።


ካልተላኩስ እንዴት መስበክ ይችላሉ? ይህም፣ “የምሥራችን የሚያመጡ እግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው!” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos