ዘፀአት 3:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ሙሴ ሁኔታውን ለመመልከት መቅረቡን እግዚአብሔር ባየ ጊዜ፣ ከቍጥቋጦው ውስጥ እግዚአብሔር “ሙሴ፣ ሙሴ” ብሎ ጠራው። ሙሴም “አቤት እነሆኝ” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ጌታም እርሱን ሊያይ እንደመጣ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር ከቁጥቋጦው መካከል፦ “ሙሴ፥ ሙሴ” ብሎ ጠራው። እርሱም፦ “እነሆኝ” አለ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሙሴም ሁኔታውን ለማየት በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር ተመለከተው፤ በቊጥቋጦውም መካከል ሆኖ “ሙሴ! ሙሴ!” ብሎ ጠራው። ሙሴም “እነሆ፥ አለሁ” አለ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እግዚአብሔር እርሱ ይመለከት ዘንድ እንደ መጣ በአየ ጊዜ እግዚአብሔር ከቍጥቋጦው ውስጥ እርሱን ጠርቶ፥ “ሙሴ! ሙሴ!” አለው እርሱም፥ “ይህ ምንድን ነው?” አለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እግዚአብሔር እርሱ ይመለከት ዘንድ እንደ መጣ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር ከቁጥቍጦ ውስጥ እርሱን ጠርቶ፦ “ሙሴ! ሙሴ ሆይ!” አለ። Ver Capítulo |