Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 2:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ቃሉን የተቀበሉትም ተጠመቁ፤ በዚያ ቀን ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች በቍጥራቸው ላይ ተጨመሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፤ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ከእነርሱ ብዙዎቹ ቃሉን ተቀብለው ተጠመቁ፤ በዚያን ቀን ሦስት ሺህ የሚያኽሉ አማኞች ተጨመሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ቃሉ​ንም ተቀ​ብ​ለው ተጠ​መቁ፤ በዚ​ችም ዕለት ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ተጨ​መሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 2:41
21 Referencias Cruzadas  

ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።


እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፣ ከእነዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።


ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ወደ ጀልባዋ ወጥቶ መረቡን ወደ ምድር ጐተተው፤ መረቡንም መቶ ዐምሳ ሦስት ትልልቅ ዓሣ ሞልተውት ነበር፤ ይህን ያህል ቢይዝም መረቡ አልተቀደደም።


በእነዚያም ቀናት፣ ጴጥሮስ መቶ ሃያ በሚሆኑ ወንድሞች መካከል ቆሞ፣


አሕዛብ ይህን በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው፤ ለጌታም ቃል ክብርን ሰጡ፤ ለዘላለም ሕይወት የተዘጋጁትም ሁሉ አመኑ።


ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ልባቸው እጅግ ተነካ፤ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም ሐዋርያት፣ “ወንድሞች ሆይ፤ ታዲያ ምን እናድርግ?” አሏቸው።


እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው፤ ጌታም የሚድኑትን በቍጥራቸው ላይ ዕለት በዕለት ይጨምር ነበር።


በመርከቡም ላይ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሰዎች ነበርን።


ያን ነቢይ የማትሰማ ነፍስ ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይታ ትጥፋ።’


ይሁን እንጂ ቃሉን ከሰሙት መካከል ብዙዎቹ አመኑ፤ የወንዶቹም ቍጥር ወደ ዐምስት ሺሕ ከፍ አለ።


ከዚህ በኋላ፣ ዮሴፍ ልኮ አባቱን ያዕቆብንና ሰባ ዐምስት ነፍስ የሚሆኑ ቤተ ዘመዶቹን በሙሉ አስመጣ።


ማንኛውም ሰው በሥልጣን ላሉት ሹማምት መገዛት ይገባዋል፤ ከእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣናት በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።


እናንተ እኛንና ጌታን መስላችኋል፤ ምንም እንኳ ብርቱ መከራ ቢደርስባችሁም፣ ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ደስታ ተቀብላችኋል።


እነዚህ በወህኒ የነበሩት ነፍሳት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ይጠብቃቸው የነበሩ እንቢተኞች ናቸው፤ በውሃ የዳኑት ጥቂት፣ ይኸውም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ።


ሁለተኛው መልአክ ጽዋውን በባሕር ላይ አፈሰሰ፤ ባሕሩም እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነ፤ በባሕሩ ውስጥ የሚኖሩ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ ሞቱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos