Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 6:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ልጆቼ እንደ መሆናችሁ መጠን ይህን አሳስባችኋለሁ፤ እናንተም በዚያው ልክ ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱልን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልጆቼ እንደ መሆናችሁ ግን ይህን እላችኋለሁ፤ እናንተም ደግሞ ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱልን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አባት ለልጆቹ እንደሚናገር ልናገርና፥ እኛ ልባችንን በሰፊው ከፍተን ስሜታችንን እንደ ገለጥንላችሁ እናንተም እንዲሁ አድርጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ ላይ ስለ​ሚ​ገ​ባኝ ብድ​ራቴ እና​ንተ ፍቅ​ራ​ች​ሁን አስ​ፉ​ልኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ልጆቼ እንደ መሆናችሁ ግን እላችኋለሁ፥ እናንተ ደግሞ ብድራት መልሳችሁልን ተስፋፉ።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 6:13
19 Referencias Cruzadas  

ልቤን አስፍተህልኛልና፣ በትእዛዞችህ መንገድ እሮጣለሁ።


ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ፣ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ አፍህን በሰፊው ክፈተው፤ እኔም እሞላዋለሁ።


ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደ ተቀበላችሁት አድርጋችሁ እመኑ፤ ይሆንላችሁማል።


ወንድሞች ሆይ፤ እለምናችኋለሁ፤ እኔ እናንተን እንደ መሰልሁ፣ እናንተም እኔን ምሰሉ። እናንተ አንዳች አልበደላችሁኝም።


የምወድዳችሁ ልጆቼ ሆይ፤ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ፣ ስለ እናንተ እንደ ገና ምጥ ይዞኛል፤


አባት ለገዛ ልጆቹ እንደሚሆን እኛም ለእያንዳንዳችሁ የቱን ያህል እንደ ሆንን ታውቃላችሁና፤


ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።


ልጆች ሆይ፤ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።


ልጆቼ በእውነት የሚመላለሱ መሆናቸውን ከመስማት የሚበልጥ ደስታ የለኝም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos