Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 2:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ስለዚህም በናያስ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ገብቶ ኢዮአብን፣ “ንጉሡ፣ ‘ከዚህ ውጣ’ ይልሃል” አለው። እርሱ ግን “አልወጣም፣ እዚሁ እሞታለሁ” አለው። በናያስም፣ “ኢዮአብ የሰጠኝ መልስ ይህ ነው” በማለት ለንጉሡ ተናገረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እርሱም ወደ ጌታ ድንኳን ሄዶ ኢዮአብን “ከዚህ ድንኳን እንድትወጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው። ኢዮአብ ግን “አልወጣም! እዚሁ እሞታለሁ!” አለ። በናያም ተመልሶ ኢዮአብ ያለውን ለንጉሡ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እርሱም ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ ኢዮአብን “ከዚህ ድንኳን እንድትወጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው። ኢዮአብ ግን “አልወጣም! እዚሁ እሞታለሁ!” አለ። በናያም ተመልሶ ኢዮአብ ያለውን ለንጉሡ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የዮ​ዳሄ ልጅ በን​ያ​ስም ወደ ኢዮ​አብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን መጥቶ፥ “ንጉሡ፦ ውጣ ይል​ሃል” አለው፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “በዚህ እሞ​ታ​ለሁ እንጂ አል​ወ​ጣም” አለ። የዮ​ዳሄ ልጅ በን​ያ​ስም፦ ተመ​ልሶ “ኢዮ​አብ የተ​ና​ገ​ረው ቃል፥ የመ​ለ​ሰ​ል​ኝም እን​ዲህ ነው” ብሎ ለን​ጉሡ ነገ​ረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 በናያስም ወደ እግዚአብሔር ድንኳን መጥቶ “ንጉሡ ‘ውጣ’ ይልሃል፤” አለው፤ እርሱም “በዚህ እሞታለሁ እንጂ አልወጣም፤” አለ። በናያስም “ኢዮአብ የተናገረው ቃል የመለሰልኝም እንዲህ ነው፤” ብሎ ወደ ንጉሡ ወሬ አመጣ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 2:30
3 Referencias Cruzadas  

ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መሆኑን ንጉሥ ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን፣ “ሂድና ግደለው!” ብሎ አዘዘው።


ንጉሡም በናያስን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “በል እንዳለው አድርግ፤ ግደልና ቅበረው፤ ኢዮአብ በከንቱ ካፈሰሰው ንጹሕ ደምም እኔንና የአባቴን ቤት አንጻን።


ከቀብጽኤል የመጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠራው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ። እርሱም እጅግ የታወቁ ሁለት የሞዓብ ሰዎችን ገደለ። እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሸፈነበት ቀን ወደ አንድ ጕድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos