Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 16:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ጌታን በማገልገል በጣም ለታወቀው ለሩፎስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እኔን እንደ ልጅዋ ትወደኝ ለነበረችው ለእናቱም ሰላምታ አቅርቡልኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በጌታ ለተመረጠው ለሩፎንና የእኔም እናት ለሆነችው ለእናቱ ሰላምታ አቅርቡልኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በጌታ ሆኖ ለታወቀ ለሩፎን ለእኔና ለእርሱም እናት ሰላምታ አቅርቡልኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ጌታ​ችን የመ​ረ​ጠው ሩፎ​ንን፥ እና​ቱ​ንም፥ ለእ​ኔም እናቴ የሆ​ነ​ች​ውን ሰላም በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በጌታ ሆኖ ለታወቀ ለሩፎን ለእኔና ለእርሱም እናት ሰላምታ አቅርቡልኝ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 16:13
12 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ “እንዲሁም ኋለኞች የሆኑ ፊተኞች ፊተኞች የሆኑትም ኋለኞች ይሆናሉ፤” አለ።


ሲሄዱም ሳሉ የቀሬና ሰው የሆነውን የእስክንድርንና የሩፎስን አባት ስምዖንን ከገጠር ወደ ከተማ ሲገባ አገኙት፤ የኢየሱስን መስቀል እንዲሸከም አስገደዱት።


የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜም፥ እኅቴም እናቴም ነው።” አለ።


እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።


ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እነኋት እናትህ!” አለው፤ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።


በጌታ አገልግሎት ለሚደክሙት ለትሩፋይናና ለትሩፎሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ አገልግሎት እጅግ ለደከመችውና በክርስቶስ ለምወዳት ለፔርሲስ ሰላምታ አቅርቡልኝ።


ለአስንክሪቶስና ለፍሌጎን፥ ለሄርሜስም፥ ለፓትሮባስም፥ ለሄርማስም፥ ከእነርሱም ጋር ላሉ ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ።


ቅዱሳንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን በፊቱ እንድንገኝ ዓለም ሳይፈጠር በክርስቶስ መረጠን።


በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው።


አሮጊቶችን እንደ እናቶች አድርገህ ተመልከታቸው፤ እንዲሁም ወጣት ሴቶችን እንደ እኅቶች አድርገህ በፍጹም ንጽሕና ተመልከታቸው።


ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆችዋ፤ ከእኔ ከሽማግሌው የተላከ መልእክት፤ እኔ በእውነት እወዳችኋለሁ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ይወዱአችኋል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos