Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 15:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ይህንንም ርዳታ በፈቃደኛነት የለገሡት ግዴታቸው በመሆኑ ነው፤ አሕዛብ ከአይሁድ ጋር የመንፈስ በረከት ተካፋዮች ከሆኑ እነርሱም በሥጋዊ በረከታቸው አይሁድን የመርዳት ግዴታ አለባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ርዳታ ለማድረግ ወድደዋል፤ በርግጥም ባለዕዳዎቻቸው ናቸው። አሕዛብ የአይሁድ መንፈሳዊ በረከት ተካፋዮች ከሆኑ፣ ያገኙትን ምድራዊ በረከት ከአይሁድ ጋራ ይካፈሉ ዘንድ የእነርሱ ባለዕዳዎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ተደስተዋልና የእነርሱ ባለ ዕዳዎች ናቸው፤ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገር አሕዛብ ተካፋዮች ከሆኑ በሥጋዊ ነገር ደግሞ ሊያገለግሉአቸው ይገባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ሰለ​ሆነ በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ አሕ​ዛ​ብን ከተ​ባ​በ​ሩ​አ​ቸው ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸው ሊረ​ዱ​አ​ቸው ይገ​ባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ወደዋልና፥ የእነርሱም ባለ ዕዳዎች ናቸው፤ አሕዛብ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ተካፋዮች ከሆኑ በሥጋዊ ነገር ደግሞ ያገለግሉአቸው ዘንድ ይገባቸዋልና።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 15:27
6 Referencias Cruzadas  

እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን፤


እንደ ጓሮ የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የሆኑ አይሁድ ተቈርጠው ቢወድቁና እናንተ እንደ ዱር የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የሆናችሁ አሕዛብ በቦታቸው ተተክታችሁ የእነርሱን ሀብትና በረከት ተካፋዮች ብትሆኑ፥


ሕግ መንፈሳዊ መሆኑን እናውቃለን። እኔ ግን የኃጢአት ባሪያ ለመሆን የተሸጥሁ ሥጋዊ ነኝ።


እኛ መንፈሳዊውን ነገር የዘራንላችሁ ከሆነ የእናንተን ሥጋዊ በረከት ብናጭድ ትልቅ ነገር መሆኑ ነውን?


ቃሉን የሚማር ሰው ከአስተማሪው ጋር መልካሙን ነገር ሁሉ ይካፈል።


እነሆ እኔ ጳውሎስ “ዕዳውን እከፍልሃለሁ” ብዬ በገዛ እጄ ጽፌ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሆኖም ስለ ሕይወትህ አንተ ራስህ እንኳ የእኔ ባለዕዳ መሆንክን እኔ ላስታውስህ አያስፈልግም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos