28 አንደበቴ ቀኑን ሙሉ ስለ ጽድቅህና ስለ ምስጋናህ ይናገራል።
28 አንደበቴ ጽድቅህን፣ ምስጋናህንም ቀኑን ሙሉ ይናገራል።
28 ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜም ምስጋናህን ይናገራል።
እኔ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ እርሱ የፈጠራቸው ሁሉ ቅዱስ ስሙን ለዘለዓለም ያወድሱ።
ሕዝቦች ስለ ክብርህና ስለ ግርማህ ታላቅነት ያወራሉ፤ እኔም ድንቅ ስለ ሆነው ሥራህ አሰላስላለሁ።
ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ምስጋናውም ዘወትር በአንደበቴ ነው።
መከራ በሚደርስብህ ጊዜ ጥራኝ፤ እኔም አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”
ምንም እንኳ ማስተዋል ቢያዳግተኝ፥ አንደበቴ ስለ ትክክለኛ ፍርድህና ስለ አዳኝነትህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።
ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ስላፈሩና ግራ ስለ ተጋቡ አንደበቴ ቀኑን ሙሉ ስለ እውነተኛ ርዳታህ ይናገራል።