Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 9:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከባዓልበሪት ቤት ሰባ ጥሬ ብር ወስደው ሰጡት፤ አቤሜሌክም በዚያ በሰባ ጥሬ ብር ዋልጌዎችንና ወሮበሎችን ቀጥሮ እንዲከተሉት አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነርሱም በኣልብሪት ቤተ ጣዖት ሰባ ሰቅል ብር ሰጡት፤ አቢሜሌክም በዚያ ወሮበሎችንና ምናምንቴዎችን ቀጠረበት፤ እነርሱም ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነርሱም በኣልብሪት ቤተ ጣዖት ሰባ ሰቅል ናስ ሰጡት፤ አቤሜሌክም በዚያ ወሮበሎችንና ምናምንቴዎችን ቀጠረበት፤ እነርሱም ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከበ​ዓ​ልም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፤ በዚ​ያም አቤ​ሜ​ሌክ ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንና አስ​ደ​ን​ጋ​ጮ​ችን ቀጠ​ረ​በት፤ እነ​ር​ሱም ተከ​ት​ለ​ውት ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከበኣልብሪትም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፥ በዚያም አቤሜሌክ ምናምንቴዎችንና ወሮበሎችን ቀጠረበት፥ እነርሱም ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 9:4
11 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በኋላ ዳዊት ቤተሰቡን ሰላም ለማለት ወደ ቤት ገባ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጣችና “የእስራኤል ንጉሥ ዛሬ ትልቅ ስም አግኝቶአል! በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ ቅሌታም ሽማግሌ እርቃኑን ገልጦአል!” አለችው።


ዘግየት ብሎም ኢዮርብዓም የማይረቡ ወሮበሎችን ሰበሰበ፤ እነርሱም በዕድሜው ማነስና በዕውቀት ያልበሰለ በመሆኑ ሊቋቋማቸው የማይችለውን የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን በረቱበት።


በጅራፍ እየተገረፉ ከአገር በመባረራቸው፥ ስማቸው የጠፋ አእምሮ ቢሶች ሆነው ይኖሩ ነበር።


ትጉህ ገበሬ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖረዋል፤ በከንቱ ምኞት መጠመድ ግን ሞኝነት ነው።


ነቢያትዋ በትዕቢት የተወጠሩና በተንኰል የተሞሉ ናቸው፤ ካህናትዋ የተቀደሰውን ያረክሳሉ፤ በሕግም ላይ ያምፃሉ።


አይሁድ ግን ቀንተው የሚበጠብጡ ሥራ ፈቶችን ከየመንገዱ ሰበሰቡና አሳደሙ። በከተማው ውስጥ ብጥብጥ እንዲነሣ አደረጉ፤ ጳውሎስንና ሲላስን አውጥተው ለሕዝቡ ለመስጠትም የኢያሶንን ቤት ከበቡ።


ዮፍታሔም ከወንድሞቹ ሸሽቶ ጦብ ተብላ በምትጠራ ምድር ኖረ፤ እዚያ ጥቂት ወሮበሎች ተሰብስበው ተከተሉት።


ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው በዓሊም የተባሉትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤ ለባዓልበሪትም ሰገዱ።


ሁሉም ወደ ወይን ተክሎቻቸው ወጥተው የወይን ፍሬ ለቀሙ፤ የወይን ጠጅ ጠምቀው ትልቅ በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም መቅደስ ገብተው በዚያ እየበሉና እየጠጡ ስለ አቤሜሌክ በማፌዝ ተናገሩ።


የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸው፥ እንዲሁም ሆድ የባሳቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እርሱ ስለ ሄዱ ብዛታቸው በድምሩ እስከ አራት መቶ ደረሰ፤ ዳዊትም የእነርሱ መሪ ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos