Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 31:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 የተፈጥሮ ሥርዓት ጸንቶ እስከ ኖረ ድረስ እስራኤል በፊቱ ሕዝብ ሆና የምትኖር መሆንዋን የሚገልጥ ተስፋ ይሰጣል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 “ይህ ሥርዐት በፊቴ ከተሻረ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚያ ጊዜ የእስራኤልም ዘር በፊቴ፣ መንግሥት መሆኑ ለዘላለም ይቀራል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 “ይህ ጽኑ ሕግ ከፊቴ ቢወገድ፥ ይላል ጌታ፥ በዚያን ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ትውልድ በፊቴ ሕዝብ የመሆኑ ነገር ለዘለዓለም ያበቃለታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 “ይህ ሕግ ከፊቴ ቢወ​ገድ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በዚያ ጊዜ ደግሞ የእ​ስ​ራ​ኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቀ​ራል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ይህ ሕግ ከፊቴ ቢወገድ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያን ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘላለም ይቀራል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 31:36
13 Referencias Cruzadas  

ሰማያት በምን ዐይነት ሥርዓት እንደሚተዳደሩ ታውቃለህን? ይህንንስ ደንብ በምድር ላይ እንዲሠራ ለማድረግ ትችላለህን?


የአገልጋዮችህ ልጆች በሰላም ይኖራሉ፤ ትውልዳቸውም በአንተ ዘንድ ጸንቶ ይኖራል።


እግዚአብሔር ሆይ! ቃልህ ዘለዓለማዊ ነው፤ በሰማይም ጸንቶ ይኖራል።


ምንጊዜም በማይፈርስ ድንጋጌ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም መሥርቶአቸዋል።


የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።


በዘመናት ሁሉ የፀሐይና የጨረቃን ያኽል ረጅም ዘመናት ይኑር።


ለያዕቆብ ልጆችን እሰጠዋለሁ፤ ይሁዳንም የተራሮቼን ርስት ወራሽ አደርገዋለሁ፤ እኔ የመረጥኩት ምድሪቱን ይይዛል፤ አገልጋዮቼም በዚያ ይኖራሉ።


እኔ ከእናንተ ጋራ ስለ ሆንኩ አገልጋዮቼ እስራኤላውያን ሆይ! እናንተ አትፍሩ፤ እናንተ በሀገራቸው እንድትበታተኑ ያደረግኹባቸውን ሕዝቦች ሁሉ አጠፋለሁ፤ እናንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋችሁም፤ ሆኖም ለማረም እቀጣችኋለሁ፤ ሳልቀጣችሁ ግን አላልፍም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እኔ ፈጽሜ እደመስሳቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos