Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 64:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የቀድሞ አባቶቻችን አንተን ሲያመሰግኑበት የነበረ፥ ቅዱስና ውብ የሆነው ቤተ መቅደስህ በእሳት ጋይቶአል፤ የሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ ፈራርሰዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና የተከበረው ቤተ መቅደሳችን፣ በእሳት ተቃጥሏል፤ ያማሩ ቦታዎቻችንም ሁሉ እንዳልነበር ሆነዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፤ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈራርሷል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አባ​ቶ​ቻ​ችን ያከ​በ​ሩት ክብ​ራ​ችን ቤተ መቅ​ደ​ስህ በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አል፤ ያማ​ረ​ውም ስፍ​ራ​ችን ፈር​ሶ​አል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፥ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈርሶአል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 64:11
21 Referencias Cruzadas  

በዚያ ቆመው ሳሉ፥ ንጉሥ ሰሎሞን ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ የእግዚአብሔር በረከት በእነርሱ ላይ እንዲወርድ እንዲህ ሲል ጸለየ፤


“በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።


እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤


ቤተ መቅደሱንና የኢየሩሳሌምን ከተማ ከነቤተ መንግሥት ሕንጻዎችና ከነሀብትዋ አቃጠለ፤ የከተማይቱንም የቅጽር ግንብ አፈራረሰ፤


“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠውን የተስፋ ቃል ፈጽሞአል፤ የሰጠውም የተስፋ ቃል እንዲህ የሚል ነው፦


እስራኤላውያን እሳት ከሰማይ ሲወርድና የእግዚአብሔርም ክብር በቤተ መቅደስ ላይ ማረፉን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው፦ “እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነው!” እያሉ ሰገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።


ካህናቱም በተመደበላቸው ቦታ ቆሙ፤ ከእነርሱም ፊት ለፊት ሌዋውያን ቆመው አስቀድሞ ንጉሥ ዳዊት አሠርቶ እግዚአብሔርን ለማመስገን ይጠቀምባቸው በነበሩት የዜማ መሣሪያዎች ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በመዘመር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ካህናቱም መለከት ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆመው ነበር።


ለጥቂት ጊዜ ቤተ መቅደስህ የቅዱስ ሕዝብህ ንብረት ነበር፤ አሁን ግን ጠላቶቻችን ረገጡት።


ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱንና በኢየሩሳሌም የነበሩ የታላላቅ ሰዎችን መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ታላላቅ ሕንጻዎችን አቃጠለ፤


የኢየሩሳሌም ሕዝብ በቀድሞ ጊዜ የነበሩአቸውን የከበሩ ነገሮች በችግራቸውና በጭንቀታቸው ቀን ያስታውሳሉ፤ እነርሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፥ አንድም ረዳት ባልነበራቸው ጊዜ፥ ጠላቶቻቸው የከተማቸውን ውድቀት ተመልክተው ተሳለቁባቸው።


እግዚአብሔር በቊጣው ጽዮንን ምንኛ አዋረዳት! ወደ ሰማይ ከፍ ብላ የነበረችውን የእስራኤልን መመኪያ ወደ ምድር ጣላት፤ በቊጣው ቀን የእግሩ ማሳረፊያ መሆንዋን ሊያስታውስ አልፈቀደም።


እግዚአብሔር መሠዊያውን ናቀ፤ መቅደሱንም ተወ፤ የቤተ መንግሥቶችዋን ቅጽሮች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤ በበዓላት ቀን እንደሚደረገው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከፍተኛ ድምፅ ተሰማ።


‘ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው አለኝ፤ የክብራችሁ ትምክሕት፥ የዐይናችሁ ተስፋና የልባችሁ ደስታ የሆነውን ቤተ መቅደሴን እንዲያረክሱ እተዋቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌም የቀሩት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በጦርነት ይገደላሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! ዘወትር ሊያዩትና ሊጐበኙት የሚወዱትን፥ የሚመኩበትንና የሚደሰቱበትን እጅግ ጽኑ የሆነውን ቤተ መቅደስ ከእነርሱ እወስድባቸዋለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም እወስዳለሁ።


መልአኩም “የሠራዊት አምላክ ሆይ! ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ሁሉ ከተቈጣህ እነሆ ሰባ ዓመቶች አለፉ፤ ምሕረት የማታደርግላቸው እስከ መቼ ነው?” ሲል ጠየቀ።


እርሱ ግን “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? በእውነት እላችኋለሁ፤ አንዳችም ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተነባብሮ ሳይፈርስ የሚቀር የለም” አላቸው።


ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos