Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 59:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነርሱ የእባብ ዕንቊላል ይቀፈቅፋሉ፤ የሸረሪት ድርም ይፈትላሉ፤ እነዚያን ዕንቊላሎች የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤ ከሚቀፈቀፈው ዕንቊላል እፉኝት ይወጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የእባብ ዕንቍላል ታቀፉ፤ የሸረሪት ድር ዐደሩ፤ ዕንቍላሎቻቸውን የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤ አንዱ በተሰበረ ጊዜም እፉኝት ይወጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የእባብን እንቁላል ቀፈቀፉ፥ የሸረሪትንም ድር አደሩ፤ እንቁላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፥ እንቁላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የእ​ባ​ብን ዕን​ቍ​ላል ቀፈ​ቀፉ፤ የሸ​ረ​ሪ​ት​ንም ድር አደሩ፤ እን​ቁ​ላ​ላ​ቸ​ው​ንም የሚ​በላ ሰው ፈጥኖ ይሞ​ታል፤ እን​ቍ​ላ​ሉም ሲሰ​በር እባብ ይወ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የእባብን እንቍላል ቀፈቀፉ፥ የሸረሪትንም ድር አደሩ፥ እንቍላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፥ እንቍላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 59:5
6 Referencias Cruzadas  

እንደ ሸረሪት ድር በሚበጠስ ነገር ይታመናሉ፤ ተስፋ የሚያደርጉበት ነገር እንኳ ቢኖር በቀላሉ ይጠፋል።


በመጨረሻ እንደ እባብ ይነድፍሃል፤ እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጭብሃል፤


የፍልስጥኤም ሕዝብ ሆይ! እነሆ የተደበደባችሁበት በትር ተሰበረ፤ ሆኖም ደስ ሊላችሁ አይገባም፤ አንድ እባብ በሞተ ጊዜ ሌላ ከእርሱ የባሰ በቦታው ይተካል፤ ከእባብ ዕንቊላል በክንፍ የሚበር እሳት የመሰለ ዘንዶ ይፈለፈላል።


በዚያም ጒጒቶች ጎጆ ሠርተው እንቊላል ይጥላሉ፤ እንቁላሎቻቸውንም ፈልፍለው በክንፎቻቸው ጥላ ሥር ይንከባከባሉ፤ አሞራዎችም ከጓደኞቻቸው ጋር በዚያ ይሰባሰባሉ።


እናንተ የእባብ ልጆች! ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ነገር መናገር እንዴት ትችላላችሁ? ሰው በአፉ የሚናገረው በልቡ ሞልቶ የተረፈውን ነው።


ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos