Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 32:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ቤተ መንግሥቱ ሳይቀር ወና ይሆናል፤ መናገሻ ከተማውም የተፈታ ምድረ በዳ ይሆናል፤ ቤቶችና የመጠበቂያ ማማዎች ይፈርሳሉ፤ የሜዳ አህዮች መራገጫና የመንጋ መሰማርያ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤ ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤ ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣ የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አዳራሹ ወና ይሆናል፥ በሰው የተጨናነቀውም ከተማ ወና ይሆናል፤ ምሽጉና ግንቡም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የበ​ለ​ጸ​ገች ከተ​ማና ቤቶ​ችዋ ምድረ በዳ ይሆ​ናሉ። የከ​ተ​ማ​ውን ሀብ​ትና ያማሩ ቤቶ​ችን ይተ​ዋሉ፤ አን​ባ​ዎ​ችም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዋሻ፥ የም​ድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመ​ን​ጎ​ችም ማሰ​ማ​ሪያ ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አዳራሹ ወና ትሆናለችና፥ የብዙ ሰውም ከተማ ትለቀቃለችና፥ አምባውና ግንቡም ለዘላለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናልና።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 32:14
27 Referencias Cruzadas  

እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤


ከዚህ በኋላ ምናሴ በዳዊት ከተማ በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን የውጪ ቅጽር ቁመት ከፍ አድርጎ ሠራ፤ ይህም ቅጽር በሸለቆው ውስጥ ከግዮን ምንጭ በስተ ምዕራብ በኩል አንሥቶ፥ በስተ ሰሜን እስከ ዓሣ ቅጽር በር የሚደርስ ሲሆን፥ በከተማይቱ አጠገብ የሚገኘውን ዖፌል ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ የሚያጠቃልል ነው፤ እንዲሁም ምናሴ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ፥ ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ የክፍለ ጦር አዛዥ መደበላቸው።


በዚህ ዐይነት የዱር አውሬዎች የሚጠጡት ውሃ ያገኛሉ፤ የሜዳ አህዮችም ጠጥተው ጥማቸውን ያረካሉ።


በሁካታና በጩኸት የተሞላሽ አንቺ ከተማ ሆይ! ሰክረው በመንገዶችሽ ላይ የወደቁት ሰዎች በሰይፍ የተገደሉ ወይም በጦርነት የሞቱ አይደሉም።


የፈረሰችው ከተማ ባድማ ትሆናለች፤ ማንም ሰው እንዳይገባበት ቤቱ ሁሉ ተዘግቶአል።


ከተማይቱ የፍርስራሽ ክምር ሆናለች፤ በሮችዋም ተሰባብረው ወድቀዋል።


ከተሞች ፈርሰው ባድማ እንዲሆኑ አድርገሃል፤ ምሽጎቻቸውንም አፈራርሰሃል፤ ጠላቶቻችን የሠሩአቸው ቤተ መንግሥቶች እንዳልነበሩ ሆነዋል፤ እስከ ዘለዓለምም እንደገና አይሠሩም።


የተመሸገችው ከተማ ፈራርሳለች፤ ባዶዋን ቀርታ ጭው ያለ ምድረ በዳ መስላለች፤ የከብቶች መሰማሪያ ስለ ሆነች በዚያ ጥጆች የዛፍ ቅርንጫፎችን እየበሉ ያርፋሉ።


የኢየሩሳሌም በሮች እርቃንዋን ሆና በልቅሶና በሐዘን እንደ ተቀመጠች ሴት ይሆናሉ።


እነሆ የሠራዊት አምላክ እንዲህ ብሎ በመሐላ ሲያረጋግጥ ሰምቼአለሁ፦ “የተዋቡ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ፈርሰው ወና ይሆናሉ፤ የሚኖርባቸው ሰውም አይገኝም።


እኔም “አቤቱ ጌታ ሆይ፥ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” ብዬ ጠየቅሁ። እርሱም “ከተሞች እስኪፈርሱ፥ ቤቶችም የሚኖርባቸው አጥተው ወና እስኪሆኑና አገሪቱም የተፈታች ባድማ እስክትሆን ድረስ ነው።


“በዚያም ቀን ግምቱ ሺህ ብር የሚሆን አንድ ሺህ ምርጥ የወይን ተክል እንዲለማ የተደረገበት ቦታ ሁሉ ኲርንችትና እሾኽ ይበቅልበታል።


የሜዳ አህዮች ከውሃ ጥም የተነሣ፥ በየኰረብታው ጫፍ ላይ ቆመው እንደ ቀበሮ ያለከልካሉ፤ ምግብ ስለማያገኙም የማየት ኀይላቸው ይቀንሳል።


በከበባውና በጦርነቱ ጥቃት ምክንያት የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ቤተ መንግሥት ይፈራርሳሉ፤


ንጉሡም በዚያው አስደብድቦ በማሠቃየት በሞት ቀጣቸው። በዚህም ዐይነት የይሁዳ ሕዝብ ከአገራቸው ተማርከው ተወሰዱ፤


ስለዚህ ተነሡ፥ በሌሊት አደጋ ጥለን የከተማይቱን ምሽጎች እናፈራርስ።”


ባትመለስ ግን እንደ ተወለደችበት ቀን እርቃንዋን አስቀራታለሁ፤ እንደ ደረቀ ባዶ ምድር አደርጋታለሁ፤ በውሃ ጥምም እገድላታለሁ።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ይሆናል።


“ከእኔ በቀር ሌላ የለም” ብላ በመዝናናትና ራስዋን በማስደሰት ትኖር የነበረችው ከተማ እንዴት የአራዊት መመሰጊያ ባድማ ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ በእጁ እየጠቈመ ያፏጭባታል።


እግዚአብሔር አምላካቸው ስለሚንከባከባቸውና ንብረታቸውን ስለሚመልስላቸው ከብቶቻቸውን ያሰማሩበት ዘንድ የባሕሩ ዳር ከይሁዳ ሕዝብ ለተረፉት ርስት ይሆናል፤ በየምሽቱም በአስቀሎና ቤቶች ያድራሉ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ኢየሩሳሌም በጠላት ወታደሮች ተከባ ባያችሁ ጊዜ ለመጥፋት እንደ ተቃረበች ዕወቁ፤


ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos