Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 12:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ስለሚቈጥራችሁ ቅጣትን ታገሡ፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ይዟችኋልና የተግሣጽን ምክር ታገሡ፤ ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፥ የተግሣጽን ቅጣት ታገሡ፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ቅጣ​ታ​ች​ሁን ታገሡ፤ ልጆቹ እንደ መሆ​ና​ችሁ ይወ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ አባቱ የማ​ይ​ቈ​ጣው ልጅ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 12:7
16 Referencias Cruzadas  

እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ስሕተት በሚፈጽምበትም ጊዜ አባት ልጁን እንደሚቀጣ እቀጣዋለሁ፤


ልጁን የማይቀጣ አይወደውም ማለት ነው፤ ልጁን የሚወድ ግን ቀጥቶ ያሳድገዋል።


የመመለስ ተስፋ ሳላቸው ልጆችህን በልጅነታቸው ቅጣቸው፤ ባትቀጣቸው ግን ለጥፋት አሳልፈህ እንደ ሰጠሃቸው ይቈጠራል።


በልጅ ልብ ውስጥ ሞኝነት አለ፤ የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያስወግደዋል።


ልጆችን መገሠጽና መቅጣት ጥበብ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ልጅ ስድ ዐደግ የሆነ እንደ ሆነ ግን እናቱን ያሳፍራል።


ልጅህን ቅጣ፤ ዕረፍትና ሰላም በማግኘት ደስ ትሰኛለህ።


በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።


ነገር ግን በኋላ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን አሁን ፈርዶ ጌታ ይገሥጸናል።


አባት ልጆቹን እንደሚገሥጽ አምላክህ እግዚአብሔርም አንተን የሚገሥጽህ መሆኑን አስተውል።


በትእዛዜ መሠረት የሚቀርብልኝን መሥዋዕትና ቊርባን ለምን ታዋርዳላችሁ? ልጆችህ ለመሥዋዕት ከሚቀርበው ምርጥ የሆነውን እየወሰዱ በመብላት ይወፍሩ ዘንድ እነርሱን ከእኔ ይበልጥ የምታከብራቸው ለምንድነው?’


የሁለቱ ልጆችህ የሖፍኒና የፊንሐስ ዕድል ፈንታ ምልክት ይሆንሃል፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።


ልጆቹ በእኔ ላይ የንቀት ተግባር ሲፈጽሙ እርሱ ስላልገሠጻቸው ቤተሰቡን ለዘለዓለም እቀጣለሁ ብዬ ነግሬዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos